የኮምቦልቻ ሪጂዮፖሊታን ቢራሮ ክፍለ ከተማ አስ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ የስራ ቡድን ለሴክተር ጽ/ቤቶችና ለቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ እቃ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃ፣ የደንብ ልብስና ጫማ፣ ብትን ጨርቅ እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ያወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የቢራሮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
የብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታዎቂያ
የኮምቦልቻ ሪጂዮፖሊታን ቢራሮ ክፍለ ከተማ አስ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ የስራ ቡድን በቢራሮ ክፍለ ከተማ ስር ላሉ ለሴክተር ጽ/ቤቶች እና ለቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 01 ቋሚ እቃ ፈርኒቸር ሎት 02 የፅህፈት መሳሪያ ሎት 03 የፅዳት እቃ ሎት 04 የደንብ ልብስ የተዘጋጁ ልብሶችና ብትን ጨርቅ ሎት 05 የደንብ ልብስ ጫማ ሎት 6 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ / 2019 የወጣውን ጨረታ በማየት ሰነዱን መግዛት የሚችሉ እንገልፃለን።
በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው
- በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸው።
- የግዥ መጠኑ ከብር 500,000/አምስት መቶ ሺህ ብር / በላይ ከሆነ ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፤
- በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 2 ላይ የተጠቀሱትና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ መክፈቻው ቀን እና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ከተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጅናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ላሉት ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ዋጋ 1% ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን የሚያስዙት የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት ብቻ መሆን ይኖርበታል።
- ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ፀንቶ ይቆያል
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር/ በኮምቦልቻ ቢራሮ ክፍለ ከተማ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 በመምጣት በመክፈል ከቀን 30 /2 /2019 ዓ.ም እስከ 9/3 2019 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት 11:30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናሉ እና ኮፒውን በተለያየ ፖስጣ በጥንቃቄ በማሸግ በኮምቦልቻ ቢራሮ ክፍለ ከተማ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ከቀኑ 30/2/2019 ዓ.ም / እስከ 9/3/2019 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት 11:30 ማስገባት ይችላሉ። የጨረታው ሳጥኑ በቀን 10/ 3/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልፅ ይከፈታል። ይሁን እንጂ የጨረታው መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነና የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ላይ በተገለፀው የመክፈቻ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነም የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም። ያልተሞላ ካለ የገኘ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይደረጋሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ጨረታውን ካወጣው አሰሪ መ/ቤት ጋር ከጨረታ መክፈቻ ከ5 አምስት ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0912044 564 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ ማድረግ ይኖርበታል - ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ።
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተ በኋላ ለ60 ቀን ይሆናል።
- ጨረታውን ለማዛባት የሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመ/ቤቱ ግዥ የማይሳተፉ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወረስ መሆኑን እንገልፃለን፤
- ግዥ ፈፃሚው አካል ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት በአሸናፊውተጫራች በውድድር የተገኘ ዋጋ ሳይቀየር በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው የአቅርቦት መጠን ላይ እስከ 20% /ሃያ በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ የሚቻል ይሆናል።
- ለሎት 04 እና ለሎት 05 በክ/ከተማው ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 5 በተቀመጠው ሳፕል/ናሙና መሰረት በማየት ሰነዱን መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን በምቦልቻ ቢራሮ ክ/ከተማ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ክ/ከተማው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የቢራሮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Kombolcha Regiopolitan Birraro Sub-City Administration buys for its sector and kebele offices by national open tender in six lots: furniture, stationery, cleaning items, uniforms and fabric, uniform shoes and electronics. Bidders need a renewed trade licence, paid tax and TIN.
