የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት (Addis Ababa City Administration Revenue Bureau-Guellele Sub City Small Tax Payers Branch Office) - 001/2019
Addis Ababa Revenues Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት (Addis Ababa City Administration Revenue Bureau-Guellele Sub City Small Tax Payers Branch Office) - 001/2019
ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ለ2019 በጀት ዓመት ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ:-
- ሎት 1:- የጽህፈት መሣሪያዎች እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት 2:- የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት 3:- ህትመት
- ሎት 4:- የደንብ ልብስ
- ሎት 5:- የተሽከርካሪ ጎማ፣ ባትሪ እና የመኪና ጥገና
- ሎት 6:- የቢሮ ወለል ምንጣፍ እና መጋረጃ
- ሎት 7:- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
- ሎት 8:- ኮምፒውተርና ተዛማጅ የአይቲ ዕቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት 9:- የህንጻ መሣሪያዎች ዕቃዎች
- ሎት 10:- የቢሮ ፈርኒቸር
- ሎት 11:- ለሰራተኞች ክበብ የሚሆኑ መጠገኛ ዕቃዎች እና የውሃ ሳኒተሪ ዝርጋታ ስራ
- ሎት 12:- ልዩ ልዩ የቢሮ ቁሳቁስ ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ መለዋወጫ ዕቃዎች
- ሎት 13:- ልዩ ልዩ የቢሮ ቁሳቁስ ጥገና
- ሎት 14:- የጀነሬተር ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ መለዋወጫ ዕቃዎች
- ሎት 15:- የጀነሬተር ጥገና
- ሎት 16:- የተለያዩ ኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች ጨምሮ፣ ፎቶኮፒ ማሽን፣ ፋክስ ማሽን፣ ፕሪንተር፣ ስካነር እና ኤሌክትሮኒክ ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ መለዋወጫ ዕቃዎች
- ሎት 17:- የተለያዩ ኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች ጨምሮ፣ ፎቶኮፒ ማሽን፣ ፋክስ ማሽን፣ ፕሪንተር፣ ስካነር እና ኤሌክትሮኒክ ጥገና
- ሎት 18:- ቆሎ
- ሎት 19:- የታሸገ ውሃ
በ2019 በጀት ዓመት ለ1ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ብቁ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ ማስረጃ የሚያቀርቡ ወይም (online የተመዘገቡ)።
- የ6 ወራት ያላለፈው የጨረታ መወዳደሪያ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በመ/ቤቱ የጨረታ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆኑን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል። ካልተጠቀሰ ዋጋው ተ.እ.ታ(VAT) እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት እንቁላል ፋብሪካ ፖሊስ መኮንኖች ክበብ አጠገብ ቃሲም ህንጻ ላይ 4ኛ ፎቅ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ጉለሌ ክ/ከተማ አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000378561829 (4054) ገቢ በማድረግ ደረሰኝ በማምጣት የግዥ አገልግሎት ቡድን ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ፋይናንሻል እና የቴክኒካል ሰነድ ዋናውን ዶክመንቱ፣ ፎቶ ኮፒውን እና የጨረታ ማስከበሪያ 2% ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ እንዲሁም የድርጅቱ ስም፣ ስልክ ቁጥራቸው፣ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን፣ የድርጅቱን ማህተም እና የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት ምድብ በመፃፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ጊዜው የሚያበቃው (በ11/3/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት እንቁላል ፋብሪካ ፖሊስ መኮንኖች ክበብ አጠገብ ቃሲም ህንፃ ላይ 4ኛ ፎቅ በግዥ አገልግሎት ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በዚያው ዕለት ከቀኑ 4:00 ሰዓት ታሽጎ፣ በዚሁ ቀን 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ የግዥ አገልግሎት ቡድን ውስጥ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 12፣13፣14፣15፣16፣17፣18 እና 19 እንዲሁም ሎት 3-ህትመት ላይ የኮንትራት ስምምነት ለሚጠየቀው ብቻ ለእያንዳንዳቸው ምድብ ብር 6000.00 /ስድስት ሺህ ብር/ ሲሆን ሌሎች ቀሪ ምድብ /ሎቶች/ ግን የጠቅላላውን ዋጋ 2% በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በሚል በማዘጋጀት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ:- በስልክ ቁጥር 011-126-50-06 ወይም 011-156-71-98 በጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የግዥ አገልግሎት ቡድን በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Addis Ababa Revenue Bureau, Gulele Small Taxpayers Branch, buys in 19 lots: stationery, cleaning, printing, uniforms, tyres and car repair, carpets, electrical, IT, building items, furniture, generator and equipment repair, kolo and bottled water. Licence, VAT, TIN, supplier list needed.
