አዲስ ጉዞ በኢትዮጵያ ለአካል ጉዳተኞች የሚሠራ ድርጅት ሲሆን በአዲሱ የሲቪል ማኅበረሰብ አዋጅ ቁጥር 1113/2019 መሠረት የተመዘገበና ለትርፍ ያልተቋቋመ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው።
አዲስ ጉዞ
የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ ጉዞ በኢትዮጵያ ለአካል ጉዳተኞች የሚሠራ ድርጅት ሲሆን በአዲሱ የሲቪል ማኅበረሰብ አዋጅ ቁጥር 1113/2019 መሠረት የተመዘገበና ለትርፍ ያልተቋቋመ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው። አዲስ ጉዞ የድርጅቱ ንብረቶች የሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ምርታማነት ማሻሻያ ፊትለፊት የሚገኙትን ባለ 20 ፊት (20 feet) ስምንት (8) ያገለገሉ ኮንቴነሮችን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለግለሰቦች ወይንም ለድርጅቶች በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም:-
- ተጫራቾች በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 05 የወጣት ማዕከል ፊት ለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ በመገኘት ዝርዝር የጨረታ ጉዳዮችን የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ተገኝተው መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ያሉ ዝርዝር ጉዳዮችን በማሟላት እና ዝርዝር ጉዳዮችን በመሙላት ያለስርዝ ድልዝ በግልፅ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ድርጅቱ ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ተገኝተው ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በ7ተኛው ቀን ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ ይዘጋል።
- ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በመግለፅ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ መፈረም የሚኖርባቸው ሲሆን ይህንኑ አድራሻቸውን የሚገልፁ ሕጋዊ ሰነድ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በአዲስ ጉዞ ድርጅት ስም አሠርተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 8ኛው የሥራ ቀን ላይ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግቢ ውስጥ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታ አከፋፈቱ አይስተጓጎልም።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911-74-05-35 በመደወል ወይንም በአካል በመገኘት መረጃ ማግኘት ይቻላል።
አዲስ ጉዞ
✨ messages.ai_summary
Addis Guzo, a non-profit working for people with disabilities, sells eight used 20-foot containers, as is, located in Lideta Sub-City Woreda 10, Addis Ababa. Open to individuals and organisations.
