Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ቂርቆስ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ


የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 01/2019 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ቂርቆስ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎትየግዥው አይነት ዝርዝርምርመራ
1.የደንብ ልብስ
2.የጽሕፈት እቃዎች
3.የፅዳት እቃዎች
4.የኅትመት
5.ኮምፒውተርና ፕሪንተር ጥገና ሰርቪስ
6.ፈርኒቸር ጥገና (ጠረጴዛ ወንበር ሼልፍ /ጥገና/)

ማሳሰቢያ

  • ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፉ የተመዘገቡበትን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃዎችና በመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ ድሀረ-ገፅ ዌብሳይት ላይ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ከኢ/ያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባችኋል፤
  • ከብር100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር በላይ ለማቅረብ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የቫት /VAT/ ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባችሁ።
  • የጨረታ ማስከበሪያ 2% በሲፒኦ /CPO/ ወይም የባንክ ጋራንቲ፤ በጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  • ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ለጨረታ ሰነዱ መግዣ ለእያንዳንዱ ሎት የግዥ ዓይነት የተቀመጠውን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በጥሬ ብር ክፍያና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመክፈል ቂርቆስ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዢ/ፋን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይቻላል።
  • ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶች ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታዎች በማሸግ ኦርጅናል እና ኮፒ የሚል ምልክት /ፅሑፍ/ በማድረግ በአንድ ትልቅ ኪ.ኪ. ፖስታ ታሽገው መቅረብ አለባቸው።
  • የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ የባንክ ጋራንቲ ወይም ጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ ኮፒ፣ እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅት ካደራጃቸው አካል የተሰጠ የዋስትና ደብዳቤ ኦርጅናል በታሸገው ፖስታ ውስጥ መካተት አለበት። በኦርጅናልና በቅጅው መካከል ያለመጣጣም ቢከሰት ኦርጅናል በባላይነት ይያዛል።
  • በመጫረቻ ሰነዱ የቀረበው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት ጀምሮ ለ60 ቀናት የፀና ይሆናል። ግምገማው ከ60 ቀናት በላይ የሚወስድ ከሆነ ጽ/ቤት እንደ አስፈላጊነቱ ግምገማው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ተጫራቾች ያቀረቡትን ዋጋ እንዲያራዝሙ የመጠየቅ መብት ያለው ሆኖ የማራዘም ፈቃደኛ ያልሆነ ድርጅት ከጨረታው ይሰረዛል።
  • የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባችኋል። ከተገለጸው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
  • ጨረታዎቹ በተጠቀሰው የመክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ የሚከፈት ይሆናል።
  • ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመርኩዞ መጫረት አይችልም።
  • ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር የሥራ ቀናት/ ክፍት ሆኖ ይቆያል በኋላ በ11ኛው ቀን 4:30 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 5:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • ጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በበዓል ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  • ተጫራቾች በጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙና እስከ ጨረታ መክፈቻ ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ በተጠየቀባቸው ናሙናዎቻቸውን ግዥ ክፍል ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  • የተጫራቾች ተግኝቶ አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ሥነ-ሥርዓትን አያስተጓጉልም።
  • ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው። ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቅሬታ መስሚያ ቀናት ቅሬታ ካለዎት በጽ/ቤቱ ማቅረብ ይቻላል። እንዲሁም ከ7 የቅሬታው መስሚያ ቀናት በኋላ ባሉት 7 የሥራ ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ ይቻላል።

ማስታወሻ

  1. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ሰነድ አንድ አካል ተደርጐ ይቆጣጠራል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የሰፈሩት ዝርዝር መረጃዎችን በተጫራቾች መመሪያ እና ሰንጠረዥ የተዘረዘሩትን ግዴታዎች በትኩረት ማንበብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ላይ ቫትን ካላካተቱ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተቆጥሮ ይወሰዳል።

አድራሻ:- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ቂርቆስ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት - ስታዲየም - ፊት ለፊት የኃ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ እንገኛለን።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር:- 251115574579

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ቂርቆስ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Addis Ababa Transport Bureau, Kirkos branch office, buys by open tender in six lots: uniforms, stationery, cleaning items, printing, computer and printer maintenance, and furniture repair. Bidders need a renewed sector trade licence, paid tax, PPA supplier registration and VAT.
Save Tender