Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline09 Dec 2026, 11:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋ 1/4 (C.P.O በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
  • opening dateምዝገባው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ፣ የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የሚገኝ ኮንዶሚኒየም ቤት የሐራጅ ሽያጭ

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለሙብት አቶ አዲስ በርሄ እና የፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ሀዳስ አበበ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/151948 በ23/7/2016 ዓ/ም በ6/09/2016 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ/04763 በ3/10/2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ክልል ውስጥ የሚገኝ በይዞታ መለያ ኮድAAO000612072783200002 የህንጻ ቁጥር B032 የቤት ቁጥር B032/02 የቤቱ ስፋት 86.01 ካ/ሜ የጋራ መጠቀሚያ 2.71 በወ/ሮ ሀዳስ አበበ ተፈሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ኮንዶሚኒየም ቤት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 3,492,197 (ሦስት ሚሊዮን አራት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ አንድ መቶ ዘጠና ሰባት ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል:: የተጫራቾች ምዝገባ 5:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል::

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለሙብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለሙብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት ¼ ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል:: ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም:: በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Federal Courts Judgment Execution Office auctions, by court order, an 86.01 m² condominium apartment (building B032, house B032/02) in Bole sub-city, Woreda 12, Addis Ababa. The buyer pays transaction tax; site visits by arrangement through the auction section. Public auction.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender

ቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የሚገኝ ቤት የሐራጅ ሽያጭ

READ MORE
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ያገለገሉ ትራንስፎርመሮች (ስክራፕ) የሐራጅ ሽያጭ

READ MORE
ቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የመኪና የሐራጅ ሽያጭ

READ MORE