Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Electric Utility Jimma Region Electric Utility Office
  • Address Jimma Town, Bosa Kito kebele, Adjacent to JUCAVM, Phone: +2510472113757
  • Website
  • Deadline26 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price700(ሰባት መቶ ብር)
  • Bid Securityበባንክ በተረጋገጠ ቼክ/CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ለሎት-1 63,000.00 (ስልሳ ሶስት ሺህ ብር ብቻ) እና ለሎት-2 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ)
  • opening dateጨረታው ከላይ በተጠቀሱት ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተገለፀው አድራሻ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል::
  • Categories Textile, Garment & Leather , Stationery Materials

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጅማ ሪጅን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለቢሮ አገልግሎት የተለያዩ ዓይነት የጽሕፈት መሳሪያዎች እና የሰራተኞች የደንብ ልብስ ስፌት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

Ethiopian Electric Utility Jimma Region Electric Utility Office


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር EEU/JR/SC&PGS/NCB-001/2019

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጅማ ሪጅን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለቢሮ አገልግሎት የተለያዩ ዓይነት የጽሕፈት መሳሪያዎች እና የሰራተኞች የደንብ ልብስ ስፌት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

ተ.ቁየዕቃው ዓይነትየሎት አይነትብዛትየጨረታ ማስከበሪያ (CPO)የጨረታው መዝጊያ ቀንየጨረታው መክፈቻ ቀን
1የጽሕፈት መሳሪያሎት-1273463,000.00ሕዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00ሕዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30
2ጃኬት እና ሱሪ ስፌትሎት-264430,000.00ሕዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00ሕዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00
ጋዎን ስፌት59
ኮት እና ሱሪ ከነ ገበሩ ስፌት148
ኮትና ጉርድ ቀሚስ ከነ ገበሩ /የሴት/ ስፌት9
ቱታ ስፌት49
  1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል::
  2. ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው::
  3. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት የማይመለስ ብር ለሎት -1 700.00 (ሰባት መቶ ብር) እና ለሎት-2 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ:: ስለሆነም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካዉንት ቁጥር EEU Jimma Region 1000156094157 ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ስሊፕ በመያዝ በጅማ ሪጅን ፋይናንስ ቢሮ ቀርበዉ ደረሰኝ እንዲቆርጡ እናሳስባለን::
  4. አድራሻ:- በጅማ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና እና ግብርና ኮሌጅ አጠገብ በሚገኘው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በጅማ ሪጅን ሰፕላይ ቼን ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 6
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውንና የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት በባንክ በተረጋገጠ ቼክ/CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ለሎት-1 63,000.00 (ስልሳ ሶስት ሺህ ብር ብቻ) እና ለሎት-2 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ) በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሕዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ከላይ በተገለፀ አድራሻ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
  6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቴክኒካል «ኦሪጅናል እና ኮፒ»፣ ፋይናንሻል «ኦሪጅናል እና ኮፒ » ባንክ ጋራንቲ «ኦሪጅናል እና ኮፒ » በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር EEU/JR/SC&PGS/NCB-001/2019 ሎት-1 ወይም ሎት-2 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ሕዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  7. ጨረታው ከላይ በተጠቀሱት ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተገለፀው አድራሻ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል::
  8. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 047-2113757 መደወል ይችላሉ::
  9. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

ጅማ ሪጅን

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Electric Utility Jimma Region seeks bidders in two lots: office stationery (2,734 items) and sewing of staff uniforms (jackets, trousers, gowns, coats, skirts and overalls). Open to firms in the sector with renewed trade licence, VAT, TIN and procurement agency registration.
Save Tender