Tender Detail

Tender Details

  • Deadline13 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceFree
  • Bid Securityተረፈ ምርት፡ ብር 300,000 CPO፤ መኪና፡ የመነሻ ዋጋ (ብር 600,000) 1/4 CPO
  • opening dateኅዳር 04 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
  • Categories Disposal Sale , Other Sales

ሠላም አዳማ ልኳንዳ ነጋዴዎች አክሲዮን ማህበር የስጋ ተረፈ ምርቶችና ያገለገለ አይሲዙ መኪና ሽያጭ (በድጋሚ የወጣ)


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሠላም አዳማ ልኳንዳ ነጋዴዎች አክሲዮን ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የስጋ ተረፈ ምርቶችና ታርጋና ሊብሬ የተመለሰ አይሲዙ መኪና አወዳድሮ ከአሸናፊው ግለሰብ ወይም ድርጅት ጋር ውል ተዋውሎ መሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁየስጋ ተረፈ ምርት ዓይነትመለኪያ
1የበሬ ቁርዝበቁጥር
2ሸሆናበቁጥር
3የጭራ ፀጉርበቁጥር
4የፍየልና የበግ ቆለጥበኪ.ግ
5የበሬ ቆለጥበኪ.ግ
6የፍየልና የበግ ቁርዝበኪ.ግ
7ቀንድበቁጥር
8አጥንትበኪ.ግ

ለተረፈ ምርት፡-

  1. ተጫራቾች ለዘርፉ የተሰጠውን የታደሰ ንግድ ፍቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 300,000 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ cpo ማስያዝ አለባቸው።
  3. ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊው ሲታወቅ ጨረታውን ላላሸነፉ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ ይሆናል።
  4. አሸናፊው ግለሰብ ወይም ድርጅት ማሸነፉ ሲረጋገጥና ውል ሲገባ የውል ማስከበሪ ብር 600,000.00 (ስድስት መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርበታል።
  5. አሸናፊው ግለሰብ ወይም ድርጅት ተረፈ ምርት የሚያጠራቅምበት የራሱን ማቀዝቀዣ ፍሪጅ ማቅረብ ይኖርበታል
  6. አሸናፊው ግለሰብ ወይም ድርጅት የራሱን የተረፈ ምርት ሰራተኛ እና ተረፈ ምርት ተረካቢ ያዘጋጃል።
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ጊዜ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  8. ጨረታው ኅዳር 04 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል። ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ታርጋና ሊብሬ የተመለሰ ያገለገለ አይሲዙ መኪና

  1. የተጫራቾች ጨረታ መነሻ ብር 600,000 (ስድስት መቶ ሺህ) ብር 1/4 (አንድ አራተኛ) CPO ማስያዝ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ጊዜ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
  3. መኪናው የሚገኘው አዳማ ከተማ ቄራ አገልግሎት ግቢ ሲሆን በስራ ሰዓት ማየት ይቻላል
  4. ጨረታው ኅዳር 4 ቀን 2019 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

አድራሻ፡- አዳማ ከተማ መብራት ኃይል አዋሽ ባንክ 2ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 2..2
ስልክ ቁጥር 022-212-84-23

ሠላም አዳማ ልኳንዳ ነጋዴዎች አክሲዮን ማህበር

✨ messages.ai_summary
Selam Adama Butchers Traders S.C is re-advertising the sale of slaughter by-products (horns, bones, hooves, tail hair, testicles and trimmings) under contract, plus a used Isuzu truck with returned plates and libre. By-product buyers must supply their own fridge and staff.
Save Tender