አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር በቃሊቲ መጋዘን የሚገኙትን የተለያዩ ሸቀጦችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
አምባሰል ንግድ ሥራዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (Ambasel Commercial Works P.L.C)
የጨረታ ማስታወቂያ
አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር በቃሊቲ መጋዘን የሚገኙትን የተለያዩ ሸቀጦችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም የዚህን ጨረታ ሰነድ በተገለፀው አድረሻ በመግዛት ማንኛውም ተወዳዳሪ ያሸነፈው አካል እቃዎችን መግዛት የሚችል ሲሆን:-
- የጨረታ አይነት:- የውሃ ፓምፕና መለዋወጫ፣ ጄኔሬተርና መለዋወጫዎች፣የተለያዩ ትራክተሮች መለዋወጫዎች በተለያዩ የጨረታ ሰነዶች በጥቅል (በሎት/ LOT) አደራጅቶ ገዢዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ነው::
- ማንኛውም ተጫራች (የተፈጥሮም ይሁን ሕጋዊ ሰውነት ያለው) በአንድ የጨረታ ሎት /Lot/አይነት ከአንድ በላይ የጨረታ ሰነድ ገዝቶ ሞልቶ ማስገባት አይችልም:: ሆኖም ሻጭ ለሽያጭ ባወጣቸው የተለያዩ ሎቶች ላይ በሁሉም ላይ በመሳተፍ ዋጋ ማቅረብ ይችላል::እያንዳንዱ ተጫራች በተመሳሳይ ሎት (በአንድ ሎት) ላይ ከአንድ በላይ የጨረታ ሰነድ ሞልቶ ማቅረቡ ከተረጋገጠ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ውጭ ይደረጋል::
- ሻጭ ይህንን ጨረታ ሰነድ በመሸጡ ምክንያት በማንኛውም ሁኔታ የውል ስምምነት እንዲፈጽም አያስገድደውም:: የውል ስምምነት እንደሆነም አይቆጠርም::
- ተጫራቾች ለመግዛት ዋጋ የሰጡበትን የንብረት/ሸቀጥ አይነት ወይም የሎት አይነት ጠቅላላ ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከጨረታ ዋጋ ሠነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች በኩባንያው ዋና መ/ቤት ወይም በሁሉም ቅርንጫፍ ጣቢያዎች ላይ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሎቶች /Lots/ በመግዛት መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የሻጭ አድራሻ ማለትም አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር ከሚገኘው አምባሰል ህንጻ 5ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 503 :አዲስ አበባ ፤በመምጣት መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ ኢትዮጵያዊ ወይም የውጭ ዜጋ ስለመሆናቸው ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ወይም ፓስ ፖርት ኮፒ እንዲሁም የንግድ ድርጅቶች ከሆኑ የንግድ ስራ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከታወጀበት እለት 22/02/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን ማለትም በ09/03/2019 ከቀኑ 11:00 ሰዓት የጨረታ ሣጥኑ ይታሸጋል:: የኩባንያው ንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ ከቅርንጫፍ የጨረታ ሰነዶች የሚመጡበትን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ማለትም በ14/03/2019 ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በሻጭ አድራሻ ማለትም አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር ከሚገኘው አምባሰል ህንጻ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 305 የጨረታ ሰነድ የመክፈት ስነ- ስርዓቱን መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: በጨረታ ሰነድ የመክፈት ስነ-ስርዓት ላይ የተጫራቾች ያለመገኘት ጨረታውን ዋጋ አያሳጣውም::
- ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ስለመሳተፍ ለሚያወጡት የትኛውም ዓይነት ወጭ (በጨረታው ተሳትፎ ቢያሸንፍ፣ ቢሸነፍ፣ በተለያየ ምክንያት ከጨረታው ውጭ ቢደረግ ወይም ጨረታው ቢሰረዝ) ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም::
- በጨረታ ሰነዶች ላይ ማብራሪያ የሚፈልግ ተጫራች በዚህ የጨረታ ሰነድ ላይ በተመለከተው የሻጭ አድራሻ የሚፈልገውን ማብራሪያ በፅሑፍ መጠየቅ ይችላል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ያለባቸው ከሻጭ ብቻ ነው:: ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በቀጥታ ከሻጭ ካለማግኘታቸው ጋር ተያይዞ ለሚከሰት ማንኛውም ዓይነት ጉድለት ወይም አለመሟላት ሻጩ ተጠያቂ አይሆንም::
- ሻጭ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር
ስልክ ቁጥር 011460701748/ 0114700751
✨ messages.ai_summary
Sale by Ambassel Trading House of various goods held at its Kality warehouse, offered in lots: water pumps and spare parts, generators and spare parts, and spare parts for various tractors. Bidders need an ID or passport copy; businesses also need a trade licence and TIN.
