የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ገበሬዎች ሁለገብ ሕብረት ሥራ ዩኒየን ሃላፊነቱ የተወሰነ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጠምባሮ ልዩ ወረዳ ላሉ አርሶ አደሮች በያዝነው 2019 ዓ/ም በሙዱላ ከተማ ከሚገኘው ማዕከላዊ መጋዘን ለሰብል አብቃይ ቀበሌያት ማራገፊያ ጣቢያዎች ለመስኖ በልግና ለመሐር የአፈር ማዳበሪያ በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል::
በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የጠምባሮ ሁለገብ የህብረት ሥራ ዩኒየን
የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ ቁጥር 001/2019
የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ገበሬዎች ሁለገብ ሕብረት ሥራ ዩኒየን ሃላፊነቱ የተወሰነ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጠምባሮ ልዩ ወረዳ ላሉ አርሶ አደሮች በያዝነው 2019 ዓ/ም በሙዱላ ከተማ ከሚገኘው ማዕከላዊ መጋዘን ለሰብል አብቃይ ቀበሌያት ማራገፊያ ጣቢያዎች ለመስኖ በልግና ለመሐር የአፈር ማዳበሪያ በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል::
ስለሆነም ከድርጅቱ ማራገፊያ ጣቢያዎች ዝርዝር መግለጫ በመውሰድ ለማጓጓዝ የሚፈልገውን የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፋልት መንገድ በኩንታል በአንድ ኪ.ሜትር ተሰልቶ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል::
በዚሁ መሠረት
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያለው/ያላት፣ የዘመኑን ግብር ከፍሎ የንግድ ፈቃድ ያሳደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለውና ህጋዊ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ ተቋም የምዝገባ ምስክር ወረቀት የሚመለስ ዋናና የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፣የተሽከርካሪዎቹን ኢንሹራንስ ዋስትና የዘመኑን ማቅረብ የሚችል
- ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ሥራውን ለመወጣቱ መልካም የሥራ አፈጻጸም ያለውና ቢችል ማቅረብ የሚችል
- የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በአንድ ወረዳ ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችልም።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጨረታ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ(CPO) 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተሽከርካሪዎች ዝርዝር ቢያንስ 1,000 ኩንታል በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችሉ መኪናዎችን የሰሌዳ ቁጥር፣የመጫን አቅም የሚያስረዳ ከመንግስታዊ አካል ወቅታዊ መረጃ የተሰጠና ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ይህ የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 2,000/ሁለት ሺህ ብር/ ብቻ በመክፈል በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ገበሬዎች ሁለገብ ኅ/ሥራ ዩኒየን ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነዱን መግዛት ይችላል።
- የጨረታው ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ማቅረብ ይችላል።
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ታትሞ ከወጣበት በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 3:30 ላይ ታሽጎ በዚያን ቀን ልክ ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒየን ጽ/ቤት ይከፈታል:: ነገር ግን 11ኛ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ለቀጣይ ሥራ ቀን ይከፈታል::
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ሙዱላ ከተማ መናኸሪያ መግቢያ አስፓልቱን ገባ ብሎ ባለው ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር፡-0916838278/0916838348
የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ገበሬዎች ሁለገብ ሕብረት ሥራ ዩኒየን ሃላፊነቱ የተወሰነ
✨ messages.ai_summary
Transport of irrigation and soil fertilizer from the central warehouse in Mudula town to distribution stations for crop-producing kebeles. Bidders need a valid sector license, tax compliance, vehicle insurance, and vehicles able to load at least 1,000 quintals at once. Partial bids within one district are not allowed.
