የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከዚህ በታች በሎት የተገለጹትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 11/19
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከዚህ በታች በሎት የተገለጹትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት:-
| ተ/ቁ | የሎት ዝርዝር | የእቃው አይነት |
| 1 | ሎት-1 | የጽሕፈት መሳሪያ |
| 2 | ሎት-2 | ኤሌክትሮኒክስ |
በመሆኑም በንግድ ዘርፉ የታደሰ ፈቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 0.5% ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 9:00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ከቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 6 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ /ፕሮፎርማ/ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ቴክኒካልና ፋይናንሺያል በተለያየ ፖስታ በማሸግ ኦርጅናልና ኮፒ በመያዝ በቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታው ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 9:30 ሰዓት ተጫራቾች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት በቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡ ነገርግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን ሳጥኑን የማሸጉም ሆነ የመከፈቱ ሥነ-ሥርዓት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ:- በስልክቁጥር 0916863812/0905454775
አድራሻ:- የዱራሜ ዞን ምክር ቤት በስተጀርባ በአዲሱ ሉዳ ቃለህይወት ህንጻ ላይ በሚገኘው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
✨ messages.ai_summary
The Central Ethiopia Regional Government Youth and Sports Bureau seeks to procure office supplies (Lot 1) and electronics (Lot 2) via open tender. Eligible bidders must hold a renewed business license and provide proof of tax registration with taxes paid.
