የአፈር ማዳበሪያ ደረቅ ጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎት (ፀዩ/001/2019) - ፀዳል ኃ/የተ/ሁለገብ ኅብረት ሥራ ዩኒየን /ዱራሜ/
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፀዳል ኃ/የተ/ሁለገብ ኅብረት ሥራ ዩኒየን /ዱራሜ/
የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ ቁጥር ፀዩ/001/2019
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ የሚገኘው ፀዳል ኃላፊነቱ የተወሰነ ሁለገብ ኅብረት ሥራ ዩኒየን የ2019/20/ የምርት ዘመን በልግና መኸር እርሻ አገልግሎት የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በሃላባ ቁሊቶ ከተማና በዶዮገና ከተማ ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ወደ ከምባታ ዞን ወረዳዎች ክላስተር ጣቢያዎች ማጓጓዝ የሚችሉ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ከዚህ በታች ከ1 እስከ 8 የተዘረዘሩ መስፈርቶች አሟልተው በመቅረብ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
- በዘርፉ ሕጋዊ፣ የታደሰ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈሉ መረጃና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል
- ከፈቃድ ሰጪ የመንግሥት መ/ቤት የሚመለስ ዋናና የማይመለስ ኮፒ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- በዘርፉ የሠራበትን የምስጋና ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል
- ጨረታውን የሚያሸንፍ ተጫራች የውል ማስከበሪያ ብር 400,000.00/አራት መቶ ሺህ/ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ብር/ በቅድሚያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በካሽ ማስያዝ የሚችል
- ተጫራቹ ለጭነት የሚያሰማራቸው ተሽከርካሪዎች ቢያንስ በአንድ ጊዜ 2000 ኩ/ል ማንሳት የሚችሉትን ዝርዝር መረጃ ፈቃድ ከሰጠው የመንግሥት መ/ቤት በተሽከርካሪ አይነት፣ የሰሌዳ ቁጥር፣ የመጫን አቅም የያዘ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ለአስተዳደር ያመች ዘንድ ማንኛውም ተጫራች በአንድ ወረዳ ካሉት ጠቅላላ ክላስተር የማራገፊያ ጣቢያዎች ውስጥ በከፊል ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ተጫራቹ ከማዕከላዊ መጋዘኖች እስከ ማራገፊያ የወረዳ ጣቢያዎች ያለውን ጠቅላላ የጠጠርና አስፋልት መንገድ ድምር ርቀት ላይ ያንድ ኪሎ ሜትር የወረዳው አማካይ ነጠላ ዋጋ በእያንዳንዱ ማራገፊያ ጣቢያ ደረጃ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ የማይመለስ 1000 ብር /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል የድርጅቱ ክብ ማህተም ያረፈበትን የጨረታ ሰነድ (የግዴታዎች ዝርዝር፣ ከማዕከላዊ መጋዘን እስከ ማራገፊያ ቦታ ያለው የጠጠርና አስፋልት መንገድ ርቀት፣ ለመንገዱ የሚያስፈልግ የተሽከርካሪ ዓይነትና የወረዳ ነጠላ አማካይ ዋጋ መሙያ) የያዘ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሰም የታሸገ ኤንቬሎፕ /ፖስታ/ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ በክብ ማህተማቸው የተረጋገጠ የጨረታ ሰነድ በድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ ቀናት በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4:00 በዩኒየኑ ጽ/ቤት በይፋ ይከፈታል፡፡ ሆኖም አስራ አንደኛው ቀን የድርጅቱ የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ጨረታው ከላይ በተገለጸው ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡ በጨረታው የሚሳተፉ ወኪል ተሳታፊዎች ከወከላቸው አካል ሕጋዊ ደብዳቤና ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አንዱ ተጫራች ሌላው ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይፈቀድም፡፡
አድራሻ፡- ከምባታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት
ስልክ 0913478832/0912355938/0992001000/0916748108
ፀዳል ኃላፊነቱ የተወሰነ ሁለገብ ኅብረት ሥራ ዩኒየን /ዱራሜ/
✨ messages.ai_summary
Dry freight transport service to haul soil fertilizer from central warehouses in Halaba Kulito and Doyogena to cluster stations in Kembata Zone districts. Bidders need a valid renewed license, tax clearance and TIN, registration certificate, prior experience, and a vehicle list showing capacity of at least 2,000 quintals at once.
