Tender Detail

Tender Details

  • Company Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
  • Address አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114420688
  • Websitehttp://www.mughercement.com.et/
  • Deadline10 Nov 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 575.00 ቫትን ጨምሮ (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 400,000.00 (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
  • Categories Vehicle tire

የተለያዩ ዓይነት የተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ጎማ ግዥ (ሙሲፋ/08/2019) - ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ

Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)


የሀገር ውስጥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ሙሲፋ/08/2019

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዓይነት የተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ያላቸው የ2018/2019 ዓ/ም ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የታክስ ከፋይ ምዝገባ ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት ገርጂ የቀድሞው ኢምፔሪያል ህንፃ ከሚገኘው የፋብሪካው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.P.O) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ድረስ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡

ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
አዲስ አበባ

✨ messages.ai_summary
Mugher Cement Factory seeks to buy various vehicle and machinery tires via open tender. Eligible bidders must hold a renewed business license, commercial registration, and 2018/2019 VAT and taxpayer registration certificates. The factory reserves the right to cancel the tender fully or partially.
Save Tender