በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች፣ የኮስሞቲክስና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የመገናኛ እና የኮምፒውተር ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች እና ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 08-2019
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች፣ የኮስሞቲክስና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የመገናኛ እና የኮምፒውተር ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች እና ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የሚሰጥ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
2. ከላይ በተራ /ቁ 1 የተገለጸው ተጫራች ማሟላት ያለበት መስፈርት ቢ.ኖርም መነሻ ዋጋቸው ከብር 2 ሚሊዮን በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የሚፈል ተጫራች ሌሎች የተዘረዘሩ መረጃዎችን ማቅረብ እንዳለ ሆኖ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም/ አያስፈልግም፡፡
3. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 18/2019 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ2:00 እስከ 6:00 የዕቃዎችን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፤
4. ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች የሚጫረቱ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 19/2019 ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ 2:00 እስከ 6:00 የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ /ብር እየከፈሉ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 መግዛት ይችላሉ፡፡
5. የግልፅ ጨረታው ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:45 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 503 ይከፈታል፤
6. ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ ለዕቃ የሰጡትን ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲፖዚት አካውንት ቁጥር 1000013088865 ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበትን የባንክ አድቫይስ ከጨረታ ሰነዱ እና ከሌሎች መረጃዎች ጋር በማያያዝ በፖስታ የተጫራቹን ስም እና አድራሻ በግልጽ በመፃፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:45 ድረስ ቢሮ ቁጥር 506 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
7. በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዙ ተጫራቾች ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
8. ያስያዙት ዋስትና ለአሸናፊ ተጫራቾች ከሽያ የሚታሰብ ሲሆን በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ባሉት ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ይሆናል፤
9. የሃራጅ ጨረታው ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 505 ይካሄዳል፡፡
10.ተጫራቾች በጨረታው ለዕቃው ከሚሰጡት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ (15%) የሚጨመር ይሆናል፡፡
11.ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ 5 /በአምስት/ ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ እና ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፤
12.ከላይ በተ/ቁ 11 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ማንሳት ያልቻሉ ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘ ዋስትና ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፡፡
13. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሳጥኑ ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ውጭ ማድረግ አይችልም፤
14. ለግልፅ ጨረታ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፤
15. በጨረታ የሚሸጥ ዕቃ በተቋሙ ከመወረሱ በፊት የዕቃው አስመጭ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበረ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፤
16 .ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የወጡ ዕቃዎችን ከቅ/ጽ/ቤቱ ሰነድ በመግዛት የወጡ ዕቃዎችን ዝርዝር በመመልከት እንዲሁም በስልክ ቁጥር 058-320-7418 ወይም 058-320-7569 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
አድራሻ፡ - በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው ዘመን ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
