Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
  • Address , Phone: 0471351716
  • Website
  • Deadline04 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityሎት1 ብር 50,000፤ ሎት 2-5 እያንዳንዳቸው ብር 5,000 (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበዕለቱ በ5:00 ሰዓት
  • Categories Office And Home Furniture , Stationery Materials , Electronics Materials

የደቡ/ምዕ/ኢት/ሕ/ክል/መ/ጠቅ/ፍ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለፍ/ቤቱ ሥራ አገ/ት ዕቃዎችን በተለያዩ ሎት ከህጋዊ አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የደቡ/ምዕ/ኢት/ሕ/ክል/መ/ጠቅ/ፍ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለፍ/ቤቱ ሥራ አገ/ት ዕቃዎችን በተለያዩ ሎት ከህጋዊ አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1 አይሲቲ እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ ሎት 2 ጽ/መሣሪያዎች ፣ ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4 ምንጣፍና መጋረጃ፣ ሎት 5 ፈርኒቸር

በዚሁ መሠረት ከተጫራቾች ተሟልቶ መቅረብ ያለበት

  1. በሥራ መስኩ ሕጋዊ እና የዘመኑ ግብር ተከፍሎ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት
  2. የቲን ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
  3. በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችል
  4. አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በተጠቀሰው ስፔስፍኬሽን መሠረት በማሟላት በራሱ ትራንስፖርት ድርጅት ወደሚያዘጋጀው እስቶር ለማቅረብ የሚችሉ
  5. በጨረታው የሚሳተፍ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በደቡ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/ገቢዎች ቢሮ አካውንት ቁጥር 1000513995777 ላይ በማስገባትና የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከጠቅላይ ፍ/ቤቱ ግዥ ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት መውሰድ የሚችሉ፡፡
  6. የጨረታው አየር ላይ የቆይታ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን በ4:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ5:00 ሰዓት የሚከፈት ሆኖ የመክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ባይሆን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ይሆናል ፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት የተለያዩ ሲሆን ሎት1 50,000.00/ሀምሳ ሺህ ብር/ ከሎት 2 እስከ ሎት 5 ላሉት ለእያንዳንዳቸው 5000.00/አምስት ሺህ ብር/ ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው ፡፡
  8. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ለእያንዳንዱ ዕቃ ግልፅ የሆነ ቴክኒካል መግለጫ ማቅረብ አለባቸው ፡፡
  9. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የመጫረቻ ሰነድ ስንጠረዥ ላይ /በድርጅቱ ፕሮፎርማ ማቅረቢያ ከሆነ በመ/ቤቱ የተዘጋጀው ቅደም-ተከተል ሳይዛባ / ዋጋ በመሙላት በአንድ ኮፒ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ በታሸገ ፖስታ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን የጨረታው ቀንና ሰዓት ከማለቁ በፊት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል ፡፡
  10. የሚከፈትበት ቦታ በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ግዥ ከፍያ ዳይሬክቶሬት ቢሮ አንደኛ ፎቅ ላይ ነው፡፡
  11. ተጫራቾች የተፈለገውን የእቃ ጥራት ወይም ብዛት አሟልቶ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  12. የተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎች/ ያለመገኘት የጨረታውን መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም ፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0471351716

የደቡ/ምዕ/ኢት/ሕ/ክል/መ/ጠቅ/ፍ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The South West Ethiopia Peoples' Region Supreme Court seeks legal suppliers for office and operational goods in five lots: ICT/electronics, stationery, cleaning supplies, carpets and curtains, and furniture. Bidders must hold a valid business license, TIN certificate, and VAT registration, and submit technical specifications.
Save Tender