በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት 29 ሰው የመጫን አቅም ያለው የሠራተኞች ሰርቪስ መኪና አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት /ደብረ ብርሃን/
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ
የጨረታ ቁጥር፡- 01/2019 ዓ.ም
በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት 29 ሰው የመጫን አቅም ያለው የሠራተኞች ሰርቪስ መኪና አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታዉ እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን እና ታክስ ክሊራንስ የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ የሰርቪስ መኪና መወዳደር ይችላሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚቀርበው ተሽከርካሪ የፈረስ ጉልበቱ የስራት ዘመኑ እና ሌሎች በጨረታ ሰነዱ የተገለፁትን መስፈርቶች አሟልተዉ መቅረብ አለባቸው፡፡
- የኪሎ ሜትር እና የነዳጅ ቆጣሪው በትክክል የሚሠራ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሰርቪስ መኪና 20,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ28 /ሃያ ስምንት/ ቀናት የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብሄራዊ ባንክ እውቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት ደ/ብርሃን በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሂሳቡን ፋይናንሻልንና ቴክኒካሉን ሰነዳቸውን በአግባቡ በመጠረዝ በፖስታ በማሸግ የተሟላ አድራሻ በመፃፍ ተዘጋጅቶ ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን 8:30 ሰአት ላይ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የዋጋ መሙያ ቅፅ ላይ ስርዝ ድልዝ እና ፍቀት ካለው ፊርማ ያለው ቢሆንም ስርዝ ድልዝ ከጨረታ ውድድር ውጪ ይደረጋል፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በፋክስ ቁጥር 011-681-38-85 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0913189073 ወይም 0987634263 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት
ደ/ብርሃን
✨ messages.ai_summary
Rental of a staff service vehicle with 29-person capacity for the North Shewa Rural Roads Maintenance Office. Bidders must have a valid trade license, TIN, and VAT registration with tax clearance; the vehicle must meet specified horsepower, age, and other requirements, with working odometer and fuel gauge.
