Tender Detail

Tender Details

  • Company South Ethiopia Police (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን)
  • Address ወላይታ ሶዶ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0461803097
  • Website
  • Deadline02 Nov 2026, 12:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200 (የማይመለስ)
  • Bid SecurityCPO ወይም የባንክ ሌተር ኦፍ ክሬዲት (መጠኑ በሰነዱ)
  • opening dateበዚሁ ዕለት 08:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Stationery Materials , Vehicle Spare Parts

የፖሊስ ደንብ ልብስ፣ ጫማ፣ አልጋ ልብስ፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የጽ/መሣሪያ፣ ጽዳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ህትመትና የግንባታ ዕቃዎች ግዥ (01) - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን

South Ethiopia Police (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን)


የግዥ ማስታወቂያ ቁጥር 01(አንድ)
የዕቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ ፤

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ አይነት የመደበኛ ፖሊስ ግራውንድ ዩንፎርም፤ የአድማ ብተና ሠራዊት ሬንጀር ልብስ፤ የአድማ ብተና ዝናብ ልብስ ፤የአድማ ብተና ፊልድ ጃኬት፤ የአድማ ብተና ስሊፒንግ ባግ፤ የአድማ ብተና ሸርጥ፤የማርችንግ ባንድ ግራውንድ ዩንፎርም፤ የቴኳንዶ ልብስ፤ የፖሊስ ዱላ፤የፖሊስ ደንብ ልብስ፤የፖሊስ ፊሽካ፤የፖሊስ ደንብ ቦቲ ጫማ፤ የወንድና የሴት ጉርድ ጫማ ፤የፖሊስ አርማ ያለው ቀበቶ፤የፖሊስ መለዮ፤የዝናብ ልብስ ፤ ፍራሽ ፤አንሶላ ከነትራስ ጨርቅ፤የውጭ ብርድ ልብስ ፤ ትራስ፤ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፤ የጽ/መሣሪያዎች ፤ የጽዳት ዕቃዎች፤የምንስ ቤት ዕቃዎች፤ የስፖርት ቲሸርትና ቁምጣ ፤ ሸራ ጫማ ፤ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፤ የተሽከርካሪ ጥገና፤የተለያዩ ዓይነት ህትመት ፤ አሰልጠኝ ቱታ ከእነ ቶርሸን ጫማ እና የግንባታ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፤-

  • ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  • የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
  • በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው
  • የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያለው
  • የታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምሥክር ወረቀትና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ሰርቲፍኬት ያለው
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  1. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ /Bid Bond/ ለሚያቀርቡት የዕቃ ዋጋ በባንክ የተመሠከረለት ቼክ/CPO/ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር አፍ ክሬዲት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከክልል ፖሊስ ኮሚሽን ግዥ እና ን/አስተዳደር ዳይክቶሬት ቢሮ ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች አንድ ተጫራች የሰጠውን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው፡፡
  4. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቅጂ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ግዥና ን/አስተደደር ዳይሬክቶሬት በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው መሠረት በግልጽ ማቅረብ አለባቸው።
  8. ጨረታ የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15ኛው ቀን በኋላ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸው ጨረታውም በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ 08:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት በኮሚሽኑ ግዥ እና ን/አስተዳደር ዳይክቶሬት ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው መሠረት በግልጽ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፍልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፤

ለተጨማሪ ማብራሪያ በ ሞባይል ስልክ ቁጥሮች 0916308743 ወይም 0916861342 እና 0917004220 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን፤ ወላይታ ሶዶ፤

✨ messages.ai_summary
South Ethiopia Police Commission seeks suppliers for police uniforms, footwear, bedding, vehicle spare parts, stationery, cleaning supplies, electronics, printed materials and construction goods via open tender. Bidders must hold a valid business license, renewed sector license, tax clearance and VAT registration, and submit a CPO bid bond.
Save Tender