Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address , Phone: ..........
  • Website
  • Deadline30 Oct 2026, 9:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200 (የማይመለስ)
  • Bid Securityበየሎቱ ከብር 4,000 እስከ 15,000 (CPO)
  • opening dateበዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰአት
  • Categories Textile, Garment & Leather , Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials

ደንብ ልብስ፣ የጽዳትና የጽህፈት እቃዎች፣ የትምህርት መርጃ፣ ቋሚ እቃ፣ ጥገናና የካፌ አገልግሎት ግዥ (10 ሎቶች, 001/2019) - የአዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

የአዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 001/2019

የአዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ለ2019 ዓ.ም በጀት አመት ቁጥር 001/2019 አገልግሎት ላይ የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡

ተ.ቁ የእቃው አይነት ሎት የሚያስያዙት የብር መጠን ፐርሰንት
1 የደንብ ልብስ 1 10,000.00 1 ፐርሰንት
2 አልባሳትና የወለል ምንጣፎች 2 4,000.00 0.8 ፐርሰንት
3 የደንብ ልብስ ስፌት 3 7,000.00 1 ፐርሰንት
4 አላቂ የጽዳት እቃዎች 4 8,000.00 1 ፐርሰንት
5 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች 5 8,000.00 0.9 ፐርሰንት
6 አላቂ የቢሮ እቃዎች 6 10,000.00 0.8 ፐርሰንት
7 የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች 7 6,000.00 0.8 ፐርሰንት
8 ቋሚ እቃ 8 15,000.00 2 ፐርሰንት
9 የጥገና ስራዎች 9 5,000.00 0.8 ፐርሰንት
10 የመምህራንና ሰራተኛ የሻይ ክበብ (ካፌ) 10 10,000.00 2 ፐርሰንት

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይፈልጋል ፡፡

  1. የንግድ ፍቃድ የምዝገባ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)ያላቸው ከ100000 /ከአንድ መቶ ሺ ብር በላይ የሆነ ግዢና አገልግሎት ተመዝጋቢ መሆን አለበት ተጨማሪ እሴት ታክስ( ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑና በአቅራቢነት የተመዘገቡ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ለካፌ ተወዳዳሪዎች ብቻ ለአንድ ጊዜ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫትን) አይጠይቅም፡፡ ...
  2. ተጫራቾች ማንኛውንም የመንግስት ታክስና የግብር ግዴታዎች ከነ መጓጓዣው በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውስጥ አካቶ ማቅረብ አለበት ...
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ(CPO)ከላይ በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት ለእያንዳንዱ በተቀመጠው የብር መጠን መሰረት ወይንም የተወዳደሩበትን የጠቅላላ ዋጋ 0.5-2 ፐርሰንት ድረስ ከላይ በየሎቱ በተቀመጠው የብርና የፐርሰንት መጠን በአዲስ ከተማ መሰናዶ ት/ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ (CPO)ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አነስተኛ እና ጥቃቅን ተወዳዳሪዎች ... ህጋዊ የሆነ ደብዳቤ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. እንዲሁም ተጫራቾች ጨረታውን እንዳሸነፉ ከተገለጸላቸው ቡሃላ በሚጠቀሰው የገንዘብ መጠን ልክ አጠቃላይ የዋጋውን 10 ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ ማምጣትና መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡ ... ሁሉም ተጫራቾች ከወዲሁ የጨረታውን ጥራት ጠብቀው መወዳደር ይጠበቅባቸዋል ፡፡
  5. ጨረታ ሰነድ በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል በግንባር በመቅረብ ለዚሁ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአካውንት ቁጥር 1000012608903 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 10 መውሰድ ይኖርባቸዋል ፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ሳንምፕል ጨረታ ከመከፈቱ 3 ቀን በፊት አስቀድሞ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ማንኛውም ሳምፕል የሚያስገባ ተወዳዳሪ በአስራ አንደኛው ቀን ቢያመጣ የማንቀበል መሆኑን ከወዲሁ አውቆ ከመከፈቱ ከ3ቀን በፊት ማስገባት እንዳለበት እያሳወቅን ሳንምፕል ለማይቀርብባቸው እቃዎች ት/ቤቱ ድረስ በመምጣት ሳምፕሉን በማየት የጥገና ስራዎችን እና በስፔሲፊኬሽን መሰረት የተጠቀሱ እቃዎችን ማቅረብ ይቻላል ... በተጨማሪ ናሙና ማቅረብ አስቸጋሪ ለሆኑ ወይንም ከብደት ላላቸው እቃዎች የሚወዳደሩበትን እቃ እስፔስፊኬሽን ወይንም ፎቶ ማቅረብ ይችላሉ፡፡ነገርግን የኮምፒዩተር ናሙና እቃው በአካል መቅረብ አለበት እንዲሁም በተጨማሪ የንግድ ቦታድረስ በመሄድ የሚታይ ይሆናል፡፡
  7. ለውድድር ያስገቡትን ናሙና ጨረታው እደተጠናቀቀ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ሳይወስዱ ግን እስከ 6 ወር ድረስ ከቆዩ ላስገቡት ናሙና እና ማንኛውንም ነገር የማንጠየቅ እና ሃላፊነት መውሰድ የማንችል መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን ...
  8. ተጫራቾች የንግድ ፍቃዳቸውን የምዝገባ ፍቃድ ቫት ቲን የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ንግድ ፍቃድ ያደሱና በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ሰነድ ሙሉ የዋጋ ዝርዝራቸውን ጭምር በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ የሁሉንም ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ዋናና ኮፒ ቴክኒካል ዋናና ኮፒ በአራት ፖስታ በማድረግ እንዲሁም ሙሉ የጨረታ ሰነዱን በያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ይመለሳል ፡፡ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት በት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታውን ሰነድ በመሙላትና በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡ ከተፈቀደው ዋናና ኮፒ ሰነዶች ቀንሶ ማስገባት አይፈቀድም፡፡ እንዲሁም ዋናላይ የሚገቡ ሰነዶች ኮፒላይ በስህተት ቢገባም ከኮፒ ውስጥ ሰነድ ወጥቶ እንደኦርጅናልተከፍቶ ሊታይለት አይቻለም ሊ.ወዳደርበትም የለውም፡፡ በሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ወይም ስርዝ ድልዝ መረጃ ተቀባይነት የለውም፡፡
  9. የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ 11 ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3.00 ሰአት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በት/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ከጠዋቱ 3.30 ሰአት ላይ ይከፈታል፡፡ ... ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው እንደተገለጸ ወዲያውኑ በመቅረብ እቃውን ከማስገባቱ በፊት የአጠቃላይ ያሸነፉባቸውን እቃ ዋጋ አስር ፐርሰንት ብር (CPO)ከላይ በተጠቀሰው ስም ከባንክ በማሰራት ውል በመዋዋል ያሸነፉባቸውን እቃዎች ግዢ ፈጻሚው መስሪያቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡ ... ማንኛውንም እቃ ከ9 ሰአት ቡሃላ ጭነው ቢመጡ የማንቀበል መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን ምክንያቱም ጥራት ኮሚቴ አይቶ ፍትሽ ስለሚያስገባ ሰአት ስለሚያጥር ነው፡፡
  10. ት/ምርት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ወይንም ከ20 ፐርሰንት በላይ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

አድራሻ አዲስ ከተማ የክፍለሃገር አውቶብስተራ አጠገብ የሚገኘው አዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112763811/15/17

በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት አዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

አጠቃላይ ማሳሰቢያ የካፌ ፤የዴክስ፤ የመስኮትና፤ የቆርቆሮ፤ የላሜራ በሮች፤የባንባ ስራዎች፤አሸንዳና ጎራንዳዎ የመሳሰሉት በአንድ ጎራ ላይ የሚሰሩ ስራዎች በሙሉ ባጠቃላይ ድምር ውጤት ነው አሸናፊው የሚገለጸው፡፡

እንዲሁም ለካፌ ተወዳዳሪዎች የቤት ኪራይ ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) እና የዴስተቢ ክፍያ በተጫራቹ የሚከፈል ነው፡፡

የካፌው አሸናፊው የሚለየው በጨረታ ሰነድ ላይ በቀረቡት ዝርዝር የአገልግሎት አቅርቦት ተጫራቾች በሞሉት ዋጋ ድምር ነው

የካፌ ተወዳዳሪ አሸናፊዎች ካሸነፉ ቡኃላ ውሉ የሚያገለግለው ለሶስት ወር ብቻ ነው ለበጀት አመቱ በየሶስት ወሩ ውሉ ይታደሳል ፡፡

የትራንስፖርት እና የጥገና አገልግሎት ስራዎች ካሸነፉ ቡሃላ ለበጀት አመቱ ሙሉ ነው፡፡

የአዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Addis Ketema General Secondary School invites suppliers to bid for uniforms, clothing and floor mats, tailoring, cleaning and office supplies, teaching aids, fixed assets, maintenance, and café services, split into 10 lots. Bidders must hold a valid business license, tax registration, and VAT registration.
Save Tender