Tender Detail

Tender Details

  • Company ፉሪ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 0910489372
  • Website
  • Deadline05 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 1,000.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 150,000.00 (CPO)
  • opening dateበዕለቱ 4፡30
  • Categories Vehicles Rent , Machinery Rental

የፉሪ ክ/ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለፉሪ ክ/ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የግንባታ ማሽነሪዎች፤ የሰው እና ደረቅ ጭነት ፤ ደብል ጋቢና ፒካፕ መኪናዎችና ተሽከርካሪዎችን ለተለያዩ አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ስለሚፈልግ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ጨረታውን እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡

ፉሪ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የፉሪ ክ/ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለፉሪ ክ/ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የግንባታ ማሽነሪዎች፤ የሰው እና ደረቅ ጭነት ፤ ደብል ጋቢና ፒካፕ መኪናዎችና ተሽከርካሪዎችን ለተለያዩ አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ስለሚፈልግ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ጨረታውን እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡

ዝርዝር ሁኔታዎች

የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከፉሪ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 1000.00 ( አንድ ሺህ ብር) በሲንቄ ባንክ ሂሳቢ ቁጥር በ "furi Sub city Finance office "A" 1064669901216 " የማይመለስ ብር ገቢ ስሊፑን/ Deposit slip/ ከፉሪ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ የጨረታ ሰነዱን ከፉሪ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፤ ንብረት አስተዳደር አወጋገድ እና ጠቅላላ አገልግሎት የሥራ ሂደት ክፍል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የተጫራቾች ግዴታዎች

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ በስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው
  4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረ CPO (ሲፒኦ) ብቻ 150,000.00 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ )ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  5. ለማሽነሪ ኪራይ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ነዳጅን፤ ቅባት፤ ጥገናን እና ሌሎች ተዛማች ወጪዎችን በተጫራቹ ድርጅት (አከራይ) የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ማሽነሪዎችን በራሳችሁ ወጪ መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ (ሥራ የሚሠራበት ቦታ) ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባችዋል፡፡
  7. የሀገር ውስጥ ተወዳዳሪዎች በአቅራቢዎች ዝርዝር (EJP) የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታው ላይ የሚያቀርቡት ማሽነሪ ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ የባለቤትነት ማስረጃ ወይም ሊብሬ ወይም ሕጋዊ የኪራይ ውል አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  9. ተወዳዳሪው አሸናፊ ከሆኑ የውል ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO (200,000.00 )ሁለት መቶ ሺህ )ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  10. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በኦርጅናል እና በኮፒ በመለየት በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን የመንግስት ሥራ ሰዓት ፉሪ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አወጋገድ እና አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት የሥራ ሂደት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  11. ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ተጨራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፉሪ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
  12. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች፡- 0910489372/0938173674 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡

ፉሪ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Furi Sub-City Finance Office invites legal bidders to rent out various construction machinery, passenger and dry cargo vehicles, double-cabin and pickup vehicles for different services. Bidders must hold a renewed trade license, TIN, and VAT registration, and be registered on the EJP supplier list.
Save Tender