Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462128588
  • Website
  • Deadline22 Oct 2026, 12:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300(ሦስት መቶ ብር)
  • Bid Securityከጠቅላላው ዋጋ 0.5% (ከ500,000 ብር በላይ ከሆነ ብር 500,000) CPO ወይም ባንክ ጋራንት
  • opening dateበተጠቀሰዉ ቀንና ቦታ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ በባለስልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል
  • Categories Vehicles Rent , Machinery Rental

መ/ቤታችን ሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2019 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ የመንገድ ግንባታና ጥገና ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚዉል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ደብል ጋቢና ሚኒ ጋቢና እና ሚኒ ባስ መኪናዎችን ብቁ ተጫራችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)


የመጀመሪያ ዙር የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር:-ሲ/መ/ባ/001/2019

የሰርቪስ መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

መ/ቤታችን ሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2019 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ የመንገድ ግንባታና ጥገና ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚዉል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ደብል ጋቢና ሚኒ ጋቢና እና ሚኒ ባስ መኪናዎችን ብቁ ተጫራችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡

ሎትየመኪናዉ አይነትብዛትጠቅላላተሽከርካሪ የሥራ ቀንየሥራ ቦታ
1ደብል ጋቢና41080በሲዳማ ክልል ሰሜናዊ ዞን
ሚኒ ጋቢና41080
2ሚኒባስ1270በዳዬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት

በዚሁ መሠረት:-

  1. ተጫራቾች በጨረታዉ መሳተፍ የሚያስችለዉን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገዉ አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት የሥራ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸዉን የሚያሳይ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00(ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር)ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር -5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (Un-conditional Bid) ከጠቅላላው ዋጋ 0.5% ሆኖ ከ500,000 ብር በላይ የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000 ብቻ CPO ወይም ባንክ ጋራንት በማሰራት ለብቻዉ በማሸግ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከባንክ የሚቀርበዉ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ180 ቀን ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
  4. የስራ ዘመናቸው ለሚኒ እና ደብል ጋቢና እ.ኢ.አ 2008 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም ሚኒባስ እ.ኢ.አ 2010 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸዉ፡፡

7. ከዚህ በፊት ከሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ዉለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምክንያት ማስጠንቀቂያ ተሰቶት ማሽነሮችን ወደ ስራ ያላስገባና ዉላቸው የተቋረጠ መኪና አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም፡፡

8. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ /Bid Security/፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ በስም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ዉስጥ ተካተዉና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ ቀን ከጧቱ 3:00 እስከ 6:00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡ ከላይ የተጠቀሰዉ ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡

9. በጨረታ ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ህጎች አለማክበር በመጫረቻ ሰነዶቻቸው በሁሉም ገጽ ላይ ማህተምና ፊርማ ያለማድረግ እና ያልተፈረመበት ሰረዝ ድልዝ ያለበት የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

10. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰዉ ቀንና ቦታ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ በባለስልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ:- ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፣ 0462-128-446

ሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን
ሀዋሳ

✨ messages.ai_summary
Sidama Roads Authority seeks eligible bidders to rent double cabina, minibus, and minibus vehicles for road construction and maintenance projects in Sidama region. Bidders must provide valid trade license, VAT registration, tax clearance, and supplier certificate. Vehicles must meet minimum age requirements.
Save Tender