Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Sugar Industry Group Omo Kuraz No-2 Sugar Factory
  • Address , Phone: 0991149485
  • Website
  • Deadline25 Oct 2026, 3:11 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityለሁለቱም ሎቶች ብር 60,000 (ሲ.ፒ.ኦ ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበአስራ ስድስተኛው ቀን
  • Categories Construction Equipment And Machinery , Machinery Rental

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ በድጋሚ የወጣ ሎት1 የኤክስካቫተር ኪራይ አገልግሎ ግዥ ሎት 2 የሎደር ኪራይ አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Sugar Industry Group Omo Kuraz No-2 Sugar Factory


በድጋሚ የወጣ የኤክስካቫተርና የሎደር ኪራይ አገልግሎት ግዥ ብሔራዊ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- አግጨ/0011/ኦኩስፋ-2/2018 ዓ.ም

  1. በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ በድጋሚ የወጣ ሎት1 የኤክስካቫተር ኪራይ አገልግሎ ግዥ ሎት 2 የሎደር ኪራይ አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል፡፡
  2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የ120 ቀን የባንክ ዋስትና //BIDBOND / በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ ተጫራቾች በመንግስት ግዥ የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር/supplier List ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በተጨማሪ የበጀት ዓመቱን ታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ውሎ በአስራ ስድስተኛ ቀን ይከፈታል፡፡ የጨረታውን መከፈቻ ትክክለኛ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ ለሁሉም የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00፣ ከሰዓት በኃላ ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00) ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት ለውድድር የቀረበ ሰነድ የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ በተጠቀሰው ነው፡-

    5.1. ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ የስኳር ፋብሪካዎች ማስተባበሪያ ቢሮ ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ 300 ሜትር ከፍ ብሎ ተዘነአ ሆስፒታል አጠገብ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ፡፡
    ስልክ ቁጥር፡ 09-91-14-94-85/0986862766/ 0940209464
    አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ

  6. ተጫራቾች ለሁለቱም ሎቶች አንድ ላይ ጨረታ የማስከበሪያ ዋስትና ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.ኦ. ወይም በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. የዕቃው ርክክብ የሚፈፀመው ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ የሚገኝበት ደቡብ ኦሞ ዞን ኃይል ውሃ ቀበሌ ነው፡፡
  8. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው፡፡
  9. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለ28 ቀናት ነው፡፡
  10. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ
Tel- 0940209464
ኃይል ውሃ
አዲስ አበባ ግዥ ማስተባበሪያ ቢሮ
Tel: 09-91-14-94-85 /0986862766
አዲስ አበባ

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ

✨ messages.ai_summary
Omo Kuraz No. 2 Sugar Factory seeks to procure excavator rental services (Lot 1) and loader rental services (Lot 2) through a national open tender. Bidders must hold a valid renewed business license, TIN, VAT registration, supplier list certificate, and tax clearance.
Save Tender