በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2019 በጀት አመት ለትራስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ አገልግሎት የሚሆን ቶታል እስቴሽን በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2019 በጀት አመት ለትራስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ አገልግሎት የሚሆን ቶታል እስቴሽን በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም፡-
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል
- የአቅራቢነት ምዝገባ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሰነዱን ከስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ሰነዱን በሚገባ በመሙላት ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል እና 2ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ሰአት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 10ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንስ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል።
- መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0467710586
የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
✨ messages.ai_summary
Silti Zone Finance Department seeks bidders for a total station for the Transport and Road Development Department. Eligible bidders must have a renewed business license, TIN, supplier registration certificate, and VAT registration.
