የጋሞጎፋ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጋሞጎፋ ገጠር መንገዶች ባለሥልጣን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጎማ አይነቶች ተወዳዳሪዎችን ሁሉ በማወዳደር ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጋሞጎፋ ገጠር መንገዶች ባለሥልጣን
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጋገመ 001/2019 ዓ.ም
የጋሞጎፋ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጋሞጎፋ ገጠር መንገዶች ባለሥልጣን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጎማ አይነቶች ተወዳዳሪዎችን ሁሉ በማወዳደር ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተገለፁትን መመዘኛዎች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
| ተ.ቁ | ዝርዝር የግማው ዓይነት | ሞዴል |
| 1 | 12 - 20 ባለ ሽቦ የፊት ከነከለመዳሪያ እና ፍላፕ | |
| 2 | 12 - 20 ባለ ሽቦ የኋላ ከነከለመዳሪያ እና ፍላፕ | |
| 3 | 20.5 – 25 ባለ ሽቦ የፊት ከነከለመዳሪያ እና ፍላፕ | |
| 4 | 20.5 – 25 ባለ ሽቦ የኋላ ከነከለመዳሪያ እና ፍላፕ | |
| 5 | 19.5 – 24 ባለ ሽቦ የኋላ ከነከለመዳሪያ እና ፍላፕ | |
| 6 | 19.5 – 24 ባለ ሽቦ የፊት ከነከለመዳሪያ እና ፍላፕ | |
| 7 | 17.5 – 25 ባለ ሽቦ የፊት ከነከለመዳሪያ እና ፍላፕ | |
| 8 | 17.5 – 25 ባለ ሽቦ የኋላ ከነከለመዳሪያ እና ፍላፕ | |
| 9 | 7.5 – 16 ባለ ሽቦ የፊት ከነከለመዳሪያ እና ፍላፕ | |
| 10 | 7.5 – 16 ባለ ሽቦ የኋላ ከነከለመዳሪያ እና ፍላፕ | |
| 11 | 14 – 24 ባለ ሽቦ የፊት ከነከለመዳሪያ እና ፍላፕ | |
| 12 | 14 – 24 ባለ ሽቦ የኋላ ከነከለመዳሪያ እና ፍላፕ | |
| 13 | 14 – 17.5 ባለ ሽቦ የፊት ከነከለመዳሪያ እና ፍላፕ | |
| 14 | 23.5 – 26 C-6 roller ባለ ሽቦ ከነከለመዳሪያ እና ፍላፕ |
- ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የአቅራቢነት ዝርዝር ከመንግስት ግዥ ማቅረብ አለበት
- ተጫራቾች በቅድሚያ በባንክ የተመሰከረለት/የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ቅጽ መሙላት ሰነዱ እንዲሞሉ፡፡ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 29/01/2019 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጋሞጎፋ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ለብሔራዊ ግልፅ ግዥ ክፍት ነው
- የዋጋ ማቅረቢያ የያዘው የጨረታ ሰነድ በአንድ ኦሪጅናልና በሁለት ኮፒ በታሸገ ኤንቬሎፕ ለጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው በ20/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋሞጎፋ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡ ከዚህ ሰዓት በኋላ ውጪ የሚመጣ የመወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበትን ጊዜ በግልጽ 28 (ሃያ ስምንት) ቀናት መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የጋሞጎፋ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን
የአበቦ ማዘዋያ ከኢትዮጵያ ሆቴል በስተጀርባ
ጋሞጎፋ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን የግዥ ፋይናንስ ክፍል ቁጥር 6
ስልክ፡- +251-47-551-1176 +251-47-551-0835 +251-47-551-1175 ፖ.ሳ.ቁ፡- 70
የጋሞጎፋ ገጠር መንገዶች ባለሥልጣን
✨ messages.ai_summary
The Gamogofa Rural Roads Authority seeks to buy various wire-type front and rear tires with rims and flaps. Bidders must have a valid business license, tax and VAT registration, supplier listing, and prior bid security. Open to national competitive bidding.
