Tender Detail

Tender Details

  • Company አቢሲኒያ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline19 Oct 2026, 5:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ሎት ከ0.5 እስከ 2% (CPO)
  • opening dateጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ 4:00 ሰዓት
  • Categories Textile, Garment & Leather , Furniture , Stationery Materials

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽሕፈት ቤት የአቢሲኒያ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2019 ዓ.ም ከታች የተዘረዘሩትን አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎችን በአንደኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

አቢሲኒያ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 001/2019

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽሕፈት ቤት የአቢሲኒያ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2019 ዓ.ም ከታች የተዘረዘሩትን አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎችን በአንደኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል (ይፈልጋል)::

ተ.ቁ የዕቃው አይነት ሎት ተ.ቁ የዕቃው አይነት ሎት ተ.ቁ የእቃው አይነት ሎት
1 ደንብ ልብስ ሎት1 6 ልዩ ልዩ መሣሪያዎች ሎት6 11 ፈርኒቸር ሎት11
2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት2 7 የመዝናኛ ክበብ ሎት7 12 ውና እና ቆሎ ሎት12
3 ህትመት ሎት3 8 የማሽነሪ ጥገና ሎት8 13 የትራንስፖርት አገልግሎት ሎት13
4 አላቂ የትምህርት እቃዎች ሎት4 9 የሕንፃ ጥገና ሎት9      
5 አላቂ የጽዳት ዕቃዎች ሎት5 10 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ሎት10      
  1. ከላይ ከተራ ቁጥር 1-13 ለተጠቀሰው እቃ እና አገልግሎት በዘርፉ ሕጋዊና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል::
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል::
  3. ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል::
  4. ቲን ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል::
  5. ተጫራች በአቅራቢነት ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆኑን በአቅራቢዎች ዝርዝር www.ppa.go.et ላይ የተመዘገበ መሆኑን የሚረጋገጥ ይሆናል::
  6. ተጫራቾች የገዙትን መደበኛ የጨረታ ሰነድ በተጫራች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች በአግባቡ ተሞልቶና በድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ ተደርጐበት ሙሉ ሰነዱ መመለስ አለበት:: ሰነዱን ያልመለሰ ከውድድር ውጭ ይሆናል::
  7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የት/ቤቱ አድራሻ ከጳውሎስ ሆስፒታል ወደ መድኃኒዓለም ት/ቤት በሚወስደው መንገድ አቢሲኒያ ፋርማሲ ፊትለፊት ባለው መንገድ ወደ ውስጥ 100 ሜ ገባ ብሎ በመገኘት ብር 200 /ሁለት መቶብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላል::
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት በተቀመጠው መሠረት ከ0.5 እስከ 2% ሲሆን ሎት ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ CPO ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 10ኛው ቀን 11:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው::
  9. ተጫራቾች እያንዳንዱን የሚሸጡበትን ነጠላ ዋጋና የጠቅላላውን ዋጋ ከነቫቱ በመግለጽ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ሙሉ አድራሻውንና የጨረታውን አይነት በመጥቀስ ከጳውሎስ ሆስፒታል ወደ መድኃኒዓለም ት/ቤት በሚወስደው መንገድ አቢሲኒያ ፋርማሲ ፊትለፊት ባለው መንገድ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ በቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
  10. ተጫራቾች በዘርፋቸው የተጠቀሰው ዕቃ በሙሉ መጫረት ይችላሉ::
  11. ሁሉም ተጫራቾች ሰነዱን ሞልተው ሲያስገቡ የዕቃውን ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው:: ናሙና ካላቀረቡ ተቀባይነት አይኖረውም::
  12. የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ የመጨረሻው ቀን በ10ኛው ቀን እስከ ቀኑ 11:30 ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 005 ውስጥ ይሆናል::
  13. ቀጣዩ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተራ ቁጥር 11 በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ተፈጻሚ ይደረጋል::
  14. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም::
  15. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አካላት የሚያቀርቡት የዋስትና ደብዳቤ የተደራጁበት ዘርፍ በግልጽ የተቀመጠና አምራች ከሆነ የሚያመርተው ዘርፍ በግልጽ የተቀመጠና ደብዳቤውን ለመፈረም ሥልጣን የተሰጠው አካል የተፈረመና የዋስትና ደብዳቤ ውል የጨረታ ማስከበሪያና ለውል ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው::
  16. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም::
  17. የጨረታ አሸናፊነት ሲረጋገጥ በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውል ለመዋዋል ፈቃደኛ የሆነ እና ዕቃውንም ለማቅረብ በግዥ ደንብ እና መመሪያ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ::
  18. ጨረታ ተወዳድሮ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ውል ለመዋዋል ሲመጡ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% cpo የውል ማስከበሪያ አሠርተው መምጣት አለባቸው::
  19. አሸናፊ ተጫራች ውል ከወሰደ በኋላ ዕቃውን በተቋሙ ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት የማቅረብ ግዴታ አለበት::
  20. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው::

ማሳሰቢያ :- ቋሚ እቃዎች በፎቶ ማስገባት አለባቸው

ስልክ ቁጥር 0112732979 /0112733515

አቢሲኒያ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

✨ messages.ai_summary
Abyssinia General Secondary School seeks suppliers for 13 lots of consumable and fixed goods and services, including uniforms, office and educational supplies, printing, cleaning items, equipment, furniture, electronics, maintenance, and transport. Bidders must be VAT/TIN registered, have a renewed license, and submit samples.
Save Tender