የቮልስዋገን ቢትል አውቶሞቢል እና ፎርድ አነስተኛ የጭነት ተሽከርካሪ የሐራጅ ሽያጭ - የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እነ ዮርዳኖስ ጋሹ እና በፍ/ባለዕዳ ልዑ ዘገየ ታምሩ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 301499 በ03/04/2017 ዓ/ም እና መ/ቁ 351983 በ29/10/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት 1ኛ.በኮ/ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ግቢ ቆሞ የሚገኝ የሰ/ቁ ኮድ 2-B33110 አ.አ ቮልስ ዋገን የቤት አውቶሞቢል (Beetle) የሐራጅ ሽያጭ መነሻ 2,080,928.64/100 ( ሁለት ሚሊዮን ሰማንያ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ስምንት ከ64/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
2ኛ. በኮ/ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ግቢ ቆሞ የሚገኝ የሰ/ቁ ኮድ 2-B 25101አ.አ ፎርድ አነስተኛ የጭነት ተሽከርካሪ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ 4,363,920 ( አራት ሚሊዮን ሶስት መቶ ስልሳ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡ ፡ ከ1/4ው አስበልጠም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C. P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +25112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
