የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለደንብ ልብስ አገልግሎት የሚውል የሴት ጫማ አምራች ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል።
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር SSNT-T645
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለደንብ ልብስ አገልግሎት የሚውል የሴት ጫማ አምራች ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች በሙያ ዘርፉ በትንሹ ሶስት ዓመት የሰሩ ፣ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተደራጁ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሚመለከተው ባለስልጣን የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ ማግኘት ይችላሉ።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T645 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ አንድ መቶ ሺህ ብር (100,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ለ90 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 9:30 በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኘው በጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
