Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Electric Utility South Addis Ababa Region
  • Address Addis Ababa, Ethiopia, Phone: +251114705377
  • Website
  • Deadline28 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price600(ስድስት መቶ ብር)
  • Bid Securityለሎት 1 ብር 120,000.00 ፤ ለሎት 2 ብር 150,000.00 (CPO ወይም ባንክ ጋራንቲ)
  • opening dateበዚሁ ቀን 8:30 ላይ
  • Categories Disposal Sale , Used Items , Electrical Materials

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ጽ/ቤት በተያዘው በጀት ዓመት የተለያየ አይነት ያገለገሉ ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Electric Utility South Addis Ababa Region


የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን የተለያየ አይነት ያገለገሉ ንብረቶችን ለመሸጥ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ደ/አ/አ/ሪ/ብ/ግ/ጨ/001/2019

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ጽ/ቤት በተያዘው በጀት ዓመት የተለያየ አይነት ያገለገሉ ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም

ተ.ቁየዕቃው ዓይነትሎትየሚገኙበት ቦታየጨረታ ማስከበሪያ (CPO)የጨረታው መዝጊያ ቀንየጨረታው መክፈቻ ቀን
1የተለያየ መጠን ያላቸው ብረታ ብረቶችሎት-1ጎፋ/ኮዬ ፕሮጀክት/ጎተራ እቃ ግምጃ ቤት120,000.00ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30
2የተቆራረጡ የአልሙኒየም ሽቦ AAC & ABCሎት-1
3የተለያዩ መጠን ያላቸው ኮፐር ኬብልሎት-1
4የተለያዩ መጠን ያላቸው ጎማዎችሎት-1
5የዘይት ብረት በርሜሎችሎት-1
6የእንጨት ምሰሶሎት-1
7ያገለገሉ ጠረጴዛ ወንበሮችሎት-1
9ያገለገሉ አሮጌ የተለያየ መጠን ትራንስፎርመሮችሎት -2ጎፋ እቃ ግምጃ ቤት150,000.00ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30

በዚህ ጨረታ ላይ ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ የሚስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ EEU-South AddisAbaba Region customer contribution አካውንት ቁጥር 1000173799946 ገቢ በማድረግ የባንክ ስሊፕ በመያዝ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን፣ግዥ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ EEU South Addis Abeba Region ተከፋይ የሚሆን ለሎት 1 ብር 120,000.00/አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር/ ለሎት 2 150,000.00/አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ተጫራቾች የከፈሉበትን ማስረጃ በመያዝ ከቢሮው ጋር በመነጋገር እቃዎቹን ባሉበት ቦታ መመልከት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ ላይ የሎት ቁጥሩና በግልጽ በመጻፍ ኮፒና ኦርጅናል ለየብቻ በማድረግ እንዲሁም ሲፒኦ/CPO/ ኦርጅናል ሰነድ ውስጥ በመክተት በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማድረግ እስከ ተጠቀሰው የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ የቀድሞ ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት ማክቤንዝ ህንጻ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ሰፕላይቼይን ግዥ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ላይ ይከፈታል፡፡
  6. ሪጅኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251-114705377 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Electric Utility South Addis Ababa Region seeks to sell various used property via open bid, including assorted metal, cut aluminum wire, copper cables, tires, oil drums, wooden poles, used tables/chairs, and old transformers. Bidders must be tax-compliant, licensed, and VAT-registered.
Save Tender