ቡና ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁ. 97/1990 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
BUNNA BANK
የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር፤ ቡባ/ሕአዳ/ሐራጅ/04/2019
ቡና ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁ. 97/1990 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
| ተ.ቁ. | የተበዳሪ ስም | የንብረት አስያዥ ስም | አበዳሪ ቅርንጫፍ | ለጨረታ የቀረበው ንብረትና የቦታ ስፋት: ለጨረታ የቀረበው ንብረት | ከተማ/ክ/ከተማ/ ቀበሌ ወረዳ/ የቤት ቁጥር | የካርታ ቁጥር | የቦታ ስፋት | የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር | ጨረታው የሚከናወንበት ቀን | ሰዓት | ጨረታው የወጣው |
| 1 | ወ/ሮ ክብርነሽ አርጋው ቶኬ | ተበዳሪ | ወላይታ ሶዶ | የመኖሪያ ቤት | ወላይታ ሶዶ ከተማ፣ አውራ-ጎዳና ግቢ ጀርባ አካባቢ የሚገኝ፤ | SN00207 0951131 | 202.856 ካ/ሜ | 1,227,355.36 | ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም | 4:00-5:00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
የሐራጅ ደንቦች፣
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በቡና ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ተጠቃሎ መክፈል አለበት:: ካልተከፈለ የተያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል:: በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል:: ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል::
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው:: ተበዳሪ እና ወኪሎቻቸው ባይገኙም ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል::
- የተጫራቾች ምዝገባ ከእያንዳንዱ የንብረት ሐራጅ መዝጊያ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል:: በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም::
- የሐራጁ አሸናፊ /ገዢ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር በዋጋው ላይ የሚታሰብ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዛወሪያ ክፍያ ጋር የተገናኙና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው /አሸናፊው/ ይከፍላል::
- በሐራጁ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ለማየት ከአበዳሪ ቅርንጫፉ ጋር በመነጋገር ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ይቻላል::
- ተጫራቹ የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በጽሑፍ ሲደርሰው ብቻ ነው::
- ጨረታው በቡና ባንክ አ.ማ ወላይታ ሶዶ ቅርንጫፍ የሚካሄድ ይሆናል::
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ ፣ ሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ስ.ቁ 011-1-58-08-63/011-1-26-36-09 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
✨ messages.ai_summary
Bunna Bank is selling a residential house in Wolaita Sodo through a public auction. Bidders must deposit one-quarter of the starting price via CPO in the bank's name. Only bidders, the borrower and the property mortgagor (or legal representatives) may attend. The winner pays all taxes and transfer fees.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
