የጽሕፈት፣ የቢሮ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሕትመት እና የካፌ አገልግሎት ግዥ (12 ሎቶች) - የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የአገሪ ቱሉ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 የአገሪ ቱሉ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ 001/2019
በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 የአገሪ ቱሉ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ለመደበኛ በጀትና የውስጥ ገቢ በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽሕፈት እና የትምህርት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት 3 አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ፣ ሎት 5 የደንብ ልብስ ስፌት፣ ሎት 6 ቋሚ የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ ሎት 7 ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 8 የሕክምና መሳሪያ ዕቃዎች፣ እና ሎት 9 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ ሎት 10 የጭነት እና የህዝብ መኪና ኪራይ አገልግሎት፣ ሎት 11 ህትመት፣ ሎት 12 የካፌ አገልግሎት፡፡
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው። ተጫራቾች ይህንኑ የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተወዳዳሪዎች በግብር ዓመቱ ተገቢውን የታክስ እና ግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ክሊራንስ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- እንዳስፈላጊነቱ የብቃት ማረጋገጫ ሰነዶች፣ ከአምራች ወይም ከአከፋፋዮች የሚሰጥ ውክልና ወይም የአሸመር ማህበር መመስረቻ ሰነድ እንዲሁም ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶች ተካተው መቅረብ አለበት።
- እንዳስፈላጊነቱ የብቃት ማረጋገጫ ሰነዶች፣ ከአምራች ወይም ከአከፋፋዮች የሚሰጥ ውክልና ወይም የአሸመር ማህበር መመስረቻ ሰነድ እንዲሁም ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶች ተካተው መቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ከዊንጌት ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ ሸጎሌ ጨፌ ሰፈር ምዕራፍ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠገብ የአገሪ ቱሉ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 የማይመለስ በየሎቱ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። በተጨማሪም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ኮፒ ከሰነዱ ጋር አያይዘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ጥራት ያለው ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ ናሙና ማቅረብ ባለባቸው ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የዕቃዎች ዝርዝርና የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማችሁን በመፃፍ ፊርማችሁንና አድራሻችሁን ማስፈርና እንደ ሚታይ አርጋችሁ ማህተም በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ከዊንጌት ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ ሸጎሌ ጨፌ ሰፈር ምዕራፍ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠገብ የአገሪ ቱሉ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከሙሉ ፋይል ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነድ ጋር እስከ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ 11ኛው ቀን በ 4፡30 በአገሪ ቱሉ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች በሰነድ የሰጡት ዋጋ መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ከውድድሩ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- የማወዳደሪያ ዋጋ ከቫት ጋር መሞላት አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታው ማስከበርያ ለሎት 1 ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ)፣ ለሎት 2 ብር 8,000 (ስምንት ሺህ ብር ብቻ)፣ ለሎት 3 ብር 3500 (ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ)፣ ለሎት 4 ብር 10,000( አስር ሺህ)፣ ለሎት 5 ብር 1000 (አንድ ሺህ)፣ ለሎት 6 ብር 5500 (አምስት ሺህ አምስት መቶ)፣ ለሎት 7 ብር 5500 (አምስት ሺህ አምስት መቶ)፣ ለሎት 8 ብር 5000 (አምስት ሺህ)፣ ለሎት 9 ብር 1000 (አንድ ሺህ)፣ ለሎት 10 ብር 1000 (አንድ ሺህ)፣ ለሎት 11 ብር 2000 (ሁለት ሺህ)፣ ለሎት 12 ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ማስያዝ ይኖርባችዋል።
- ት/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ የዕቃውን ብዛት ከውል በፊት 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
- አሸናፊው ድርጅት ዕቃዎቹን እስከ አገሪ ቱሉ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት አጠቃሎ ማስገባት አለበት።
- በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጃችሁ መወዳደር የምትችሉት ባመረታችሁት ምርት ወይም እሴት በጨመራችሁት ብቻ ሲሆን ከዚህ ውጪ ግን እንደ ማንኛውም እጩ ተወዳዳሪ የጨረታ ሰነድ መግዛትና የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ መወዳደር የምትችሉ ይሆናል።
- ተጫራቾች ዕቃውን እስከ 6 ወር 25% ባሸነፉበት ዋጋ መስሪያ ቤቱ ለመጨመር ቢጠይቅ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለበት ውድቅ ይሆናል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251991119100 / 0112307230 / 0112307301
በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ከዊንጌት ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ ሸጎሌ ጨፌ ሰፈር ምዕራፍ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠገብ
በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 የአገሪ ቱሉ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Supply of stationery and educational materials, consumable office and cleaning supplies, uniforms and tailoring, furniture, electronics, medical equipment, electronics repair, vehicle rental, printing, and café services, in 12 lots. Bidders need a valid trade license, business registration, VAT registration, tax clearance, and samples.
