Tender Detail

Tender Details

  • Company የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን
  • Address ከቄራ ወደ ሜክሲኮ በሚወስደው መንገድ ላንድማርክ ሆስፒታል ጎን ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 557 2734
  • Website
  • Deadline20 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityበሎት: ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት (CPO ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው ባንክ ጋራንቲ)
  • opening dateተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8:30 መ.ሠ.ፋ ግዥ ክፍል ይከፈታል።
  • Categories Stationery Materials , Car Decoration Materials , Tire And Spare Parts , Cloth And Shoes

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን በስሩ ለሚገኙት ክፍሎች ከዚህ በታች በሎት የተገለፁትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር መ.ሠ.ፋ/ብ.ግ.ጨ-002/2019

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን በስሩ ለሚገኙት ክፍሎች ከዚህ በታች በሎት የተገለፁትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • Lote 1 የጽሕፈት መሣሪያ
  • Lote 2 የጽዳት እቃዎች
  • Lote 3 የሠራተኛ ደንብ ልብስ
  • Lote 4 የተሽከርካሪ ጎማና ባትሪ

በዚህም መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው የምትሳተፉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ/ VAT Registration Certificate/፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡ እና የቲን ሰርተፊኬት፣ የብቃት ሰርተፊኬት፣ tax clearance certificate፣ የመንግስት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር በየሎቱ 500/ አምስት መቶ/ ብር በመክፈል መ.ሠ.ፋ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 015 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማለትም
    ሎት 1ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
    ሎት2ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
    ሎት3ብር 50,000 / ሃምሳ ሺህ ብር/
    ሎት4ብር 50,000 / ሃምሳ ሺህ ብር/
    በባንክ በተመሰከረለት /ሲ.ፒ.ኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ብቻ በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ስም ከጨረታው ኦርጅናል ቴክኒካል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ሰነዶቻቸውን ኦሪጂናል እና አንድ አንድ ኮፒ ለየብቻ ለይቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቢሮ ቁጥር 015 በመምጣት መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ እንዲሁም ተያያዥ ዶክመንቶች ማቅረብ አለባቸው።
  5. ይህ ጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ልክ 8:00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8:30 መ.ሠ.ፋ ግዥ ክፍል ይከፈታል።
  6. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሁፍ የሚገለጽላቸው እና የውል ስምምነት የሚፈፅሙ ይሆናል።
  7. በጨረታ ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  8. ፋውንዴሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡-

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው ላንድ ማርክ ሆስፒታል አጠገብ

ስልክ ቁጥር፡- 0115572752 / 0910993814

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን

✨ messages.ai_summary
The Defense Forces Foundation seeks to buy stationery, cleaning materials, staff uniforms, and vehicle tires and batteries through open tender for its units. Bidders must hold a valid trade license, tax and VAT registration, TIN, competency and tax clearance certificates, and a government procurement agency certificate.
Save Tender