በድጋሚ የወጣ የባኮ ሎደር(ባለ ጎማ እስካቫተር) እና ገልባጭ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019
Afar Salt Production Share Company
የጨረታ ማስታወቂያ
በድጋሚ የወጣ የባኮ ሎደር(ባለ ጎማ እስካቫተር) እና ገልባጭ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019
የአፋር ጨው ማምረቻ አክሲዮን ማህበር አፍዴራ ለሚገኘው የጨው ማምረቻ ሳይት አጠቃላይ ስፋታቸው በግምት 40,000.00 (አርባ ሺህ) ስኴር ሜትር በሆኑ ክርስታላይዜሽን ፖንዶች ውስጥ ተከማችቶ የሚገኘውን ግምቱ 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) ኪዩቢክ ሜትር የጨው ምርት መቆፈር መከስከስ፣ መሰብሰብ፣ ማጓጓዝ ይፈልጋል ። ስለሆነም ባኮ ሎደር (ባለ ጎማ እስካቫተር) ለመቆፈር ፣ ገልባጭ ለመጓጓዝ በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የሆኑ በዘርፍ የተሠማሩ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ዋናው መ/ቤት በሚገኘው ቢሮ ወይም አፍዴራ ከሚገኘው የማምረቻ ፕላንት ጽ/ቤት ገንዘብ ቤት በመቅረብ እና ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ) በመክፈል የጨረታ ሠነዱን በመግዛት መጫረት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- የጨረታ ሠነዱን ከዋና መ/ቤት አዲስ አበባ ይሁን አፍዴራ የገዙ ተጫራቾች በጨው ማምረቻ ሳይት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቹ ከጨረታ ሠነዳቸው ጋር ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ከማንኛውም ባንክ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በአፋር ጨው ማምረቻ አክሲዮን ማህበር /AFAR SALT PRODUCTION S.C/ ስም ማሲያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በአንድ ካሬ ሜትር ስፋት ላይ የሚገኘውን ጨው ቆፍረው ፣ከስክሰውና ሰብስበው ለመጫን ዝግጁ የሚያደርጉበትንና የሚያጓጉዙበት ዋጋ ከጨረታ ሠነድ ጋር በተያያዘ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሙላት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚዘጋው በ15ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ሆኖ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአፍዴራ በጨው ማምረቻ ሳይት በሚገኘው ቢሮ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል ሆኖም የመክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
አድራሻ ፡- አፋር አፍዴራ 0981-820782
አዲስ አበባ ፡-22 ማዕድን ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ ዮናስ ጨርጨር ሥጋ ቤት ፊት ለፊት
ሥልክ ቁጥር 0951 -80 20 23
የአፋር ጨው ማምረቻ አክሲዮን ማህበር
✨ messages.ai_summary
Afar Salt Production Share Company seeks bidders to rent a wheeled backhoe loader and dump truck to excavate, break up, collect and transport an estimated 250,000 cubic meters of salt from crystallization ponds covering about 40,000 square meters at its Afdera salt production site. Eligible bidders must hold a valid renewed business license and be VAT-registered.
