በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ቦሌ/ክ/ከ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት 001/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
- ሎት አንድ:-የተለያዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት ሁለት:-የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት ሦስት:- ልዩ ልዩ ቋሚ አላቂ ዕቃዎች
- ሎት አራት:-የተለያዩ የደንብ ልብሶች
- ሎት አምስት:-የሕትመት ሥራዎች
- ሎት ስድስት :-ቋሚ ዕቃዎች
- ሎት ሰባት :- የተለያዩ የመኪና ማስዋቢያ ዕቃዎች
- ሎት ስምንት:-የውሃ እና ቆሎ ግዥ
- ሎት ዘጠኝ:-አጠቃላይ የፅዳት አገልግሎት
- ሎት አስር:-የተለያዩ ኮምፒውተር ፣ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን ጥገና እንዲሁም የጥገና መለዋወጫ ዕቃዎች
- ሎት አስራ አንድ:-የኤሌክትሪክ ፣የጀኔሬተር እና የቢሮ እቃዎች ጥገና እና የጥገና መለዋወጫ ዕቃዎች
- ሎት አስራ ሁለት:- የቢሮ ወንበር፣ ጠረጴዛ የመሳሰሉ እና የህንጻ በሮች፣ መስኮቶች ፣የመፀዳጃ ቤት እቃዎች ጥገና እና የጥገና መለዋወጫ ዕቃዎች
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ከሚወዳደሩበት ዕቃ ወይንም አገልግሎት ግዥ ጋር ለመወዳደር ተያያዥነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃዎችን (ክሊራንስ) ከግብር አስገቢው መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት ግዥ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሀገር ውስጥ የድጋፍ አቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት (በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት) የተደራጁ መሆኑን እና ከአደራጃቸው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ለአጠቃላይ ከሎት አንድ እስከ ሎት አስራ ሁለት 2% ለተወዳደሩበት ሎቶች በባንክ በተመሰከረለት (C.P.O) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ C.P.O መሰራት ያለበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለቦሌ ክ/ከ/አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በሚል አድራሻ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜ እስከ 11:00 ሰዓት ጨምሮ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መከፈቻው ቀን ድረስ አንበሳ ጋራዥ በስተጀርባ ከሚገኘው የቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ከግዥ ቡድን አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያጠቃለለ እና ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጥንቃቄ በማሸግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይገባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በመ/ቤቱ አዳራሽ 4ተኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ እያንዳንዱ ተጫራች ለጨረታ መወዳደር በሚቀርብበት ወቅት ኦርጅናል እና ኮፒ የዋጋ ማቅረቢያ /ዝርዝር/በተለያየ ፖስታ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ኮፒ እና ኦርጅናል ተለይቶ በፖስታው ውጫዊ ገጽ መጻፍ አለበት፡፡
- ሰነዱን በሚመልስበት ወቅት ስልጣን ባለው አካል መፈረምና የድርጅቱ ማህተም መደረግ አለበት ነገር ግን የሚፈርመው አካል ተወካይ ከሆነ የውክልና ማስረጃ መያያዝ አለበት፡፡
- አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የአሸናፊነት ደብዳቤ እንደደረሰው የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር ፐርሰንት) C.P.O በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም ዕቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ናሙናዎችንም ለንብረት አስተዳደር ክፍል ማስረከብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት መቆየት አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
ስልክ ቁጥር:- 0116-39-42-45
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
የቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Procurement of assorted office supplies, cleaning materials, consumables, uniforms, printing works, fixed assets, car wash items, water and corn, general cleaning services, and maintenance of computers, printers, copiers, electrical and generator equipment, office furniture, and building fixtures. Bidders must have a renewed business license, tax clearance, VAT registration, and supplier registration.
