Tender Detail

Tender Details

  • Company የሁሩታ ሄጦሳ ዴራ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
  • Address ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 02 23 35 00 46
  • Website
  • Deadline21 Oct 2026, 10:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400(አራት መቶ ብር)
  • Bid Securityለውሃ ቧንቧ ማገጣጠሚያ መሣሪያዎች ብር 20,000.00፤ ለሌሎቹ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 15,000.00 (C.P.O.)
  • opening dateበ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ በ5:00 ሰዓት
  • Categories Water Pipes And Fittings , Stationery Materials , Electronics Materials

የሁሩታ ሄጦሳ ዴራ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ2019 የበጀት ዓመት በድርጅታችን ለሚገኙ ለቅርንጫፍ ውሃ አገልግሎታችን የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች ፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ ለውሃ እና ቧንቧ መገጣጠሚያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሁሩታ ሄጦሳ ዴራ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁ-01/2019

የሁሩታ ሄጦሳ ዴራ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ2019 የበጀት ዓመት በድርጅታችን ለሚገኙ ለቅርንጫፍ ውሃ አገልግሎታችን የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች ፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ ለውሃ እና ቧንቧ መገጣጠሚያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

  1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ እና በፌደራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ለውሃ ቧንቧ መገጣጠሚያ መሣሪያዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ)፣ በሁሩታ ሄጦሳ ዴራ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ስም የኦሮሚያ ህብረት ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000004711258 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀን ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፣ ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4:30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ5:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች ለውሃ ቧንቧ ማገጣጠሚያ መሣሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) እንዲሁም ኤሌክትሮኒክስ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ) በአቅራቢያቸው በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ (C.P.O.) ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ከምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ኢተያ ከተማ ውስጥ በሚገኘው በሁሩታ ሄጦሳ ዴራ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁጥር 0223350046, 0223350470, 0910422263 ይጠይቁ፡፡

የሁሩታ ሄጦሳ ዴራ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Huruta Hethosa Dera Water Supply and Sewerage Service Enterprise seeks suppliers for office electronics, stationery, cleaning materials, staff uniforms, and water pipe fittings for its branch water services. Bidders must have a valid trade license, tax registration, VAT registration, and supplier certificate.
Save Tender