Tender Detail

Tender Details

  • Company አፍሪካን ሌክስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግል/ማህበር
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline09 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300(ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 30,000.00 (ሠላሳ ሺህ ብር) CPO ወይም የባንክ ዋስትና
  • opening dateመስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡15 ሰዓት
  • Categories Disposal Sale , Car Decoration Materials , Tire And Spare Parts

ድርጅታችን አፍሪካን ሌክስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግል/ማህበር የቶዮታ፣ ኪያ፣ ፎርድ፣ ኒሳን፣ ቤኤም ደብሊው እና ላንድሮቨር የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን (Spare Parts) በክፍት ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

አፍሪካን ሌክስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግል/ማህበር


በድጋሚ የወጣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን አፍሪካን ሌክስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግል/ማህበር የቶዮታ፣ ኪያ፣ ፎርድ፣ ኒሳን፣ ቤኤም ደብሊው እና ላንድሮቨር የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን (Spare Parts) በክፍት ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ በዘርፉ ልምድ ያላቸው ወይም ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡

  1. ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን የጨረታ መመሪያ እና መመዘኛዎች የሚያሟላ ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች መወዳደር ይችላል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቱሪስት ቅርንጫፍ (አካውንት ቁጥር 1000003782968) በመክፈል እና የገቢ ደረሰኝ ይዘው በመቅረብ የድርጅታችን ዋና መስሪያ ቤት የሚገኝበት አምስት ኪሎ አንበሳ ግቢ ጀርባ አስተዳደር መምሪያ በአካል በመቅረብ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር፣ የምስክር ወረቀት ካለ ወይም የታደሠ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሠላሳ ሺህ ብር) በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ደብዳቤ የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. የጨረታ ዋጋው ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡
  6. ተጫራቾች እቃዎቹን አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 1372 አምስት ኪሎ ከአንበሳ ግቢ ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት መጋዘን በመገኘት የንብረቶቹን ሁኔታ በአካል መመልከት ይችላል።
  7. ግልጽ ጨረታው መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ጠዋት 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች እቃዎቹ ባሉበት ቦታ በአካል በመገኘት እና እቃዎቹን በአግባቡ ተመልከተው ዋጋ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- አፍሪካን ሌክስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግል/ማህበር አስተዳደር መምሪያ ስልክ ቁጥር 0911244680 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አፍሪካን ሌክስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግል/ማህበር

✨ messages.ai_summary
African Lex Ethiopia invites bids for the open sale of spare parts for Toyota, Kia, Ford, Nissan, BMW and Land Rover vehicles. Experienced or interested individuals and companies may bid. Bidders must submit a renewed business license, TIN, and ID or certificate, and must physically inspect the items.
Save Tender