Tender Detail

Tender Details

  • Company በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address ቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አዲስ አበባ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ጊዮርጊስ አ.አ ፖሊስ ኮሚሽን ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-11-48-00
  • Website
  • Deadline13 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Security10,000 (አስር ሺህ ብር) CPO፤ ለሕትመት 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) CPO
  • opening dateበዚያው ቀን ከረፋዱ 4:30
  • Categories Laboratory Equipment And Chemicals , Stationery Materials , Electronics Materials

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የቢሮ ዕቃና የትምህርት መሣሪያዎች፣ የጥገና ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ሕትመት፣ ቋሚ ዕቃ፣ የፎቶ ኮፒ ማሽን ጥገና፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የላቦራቶሪ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/19

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የቢሮ ዕቃና የትምህርት መሣሪያዎች፣ የጥገና ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ሕትመት፣ ቋሚ ዕቃ፣ የፎቶ ኮፒ ማሽን ጥገና፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የላቦራቶሪ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ በመንግሥት ግዢ ዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀትና የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. የጨረታ ሰነዱ በሁለት ፖስታዎች ዋና /original/ እና ቅጂ /copy/ ኤንቬሎፕ ታሽጎ በጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታው ማስረከቢያ ሰዓት ከመድረሱ በፊት በቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል መግባት ይኖርበታል።
  3. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩ ዕቃዎች ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በ CPO ከዋናው (original) የጨረታ ሠነድ ውስጥ አድርጎ ማቅረብ ይኖርበታል።
  5. ለሕትመት ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) በ CPO ከዋናው (original) የጨረታ ሠነድ ውስጥ አድርጎ ማቅረብ ይኖርበታል።
  6. ተወዳዳሪዎች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት መሥሪያ ቤታችን በግንባር በመገኘት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ።
  7. ጨረታው ማስታወቂያው በወጣ በ11ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከረፋዱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  8. የጨረታ ሠነድ መቀበያ ሰዓት ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
  9. መስሪያ ቤቱ ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በአሸናፊው ተጫራች የቀረበው በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% /ሃያ በመቶ/ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
  10. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው የዕቃ ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ ያህል በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርበታል።
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ጊዮርጊስ አ.አ ፖሊስ ኮሚሽን ፊት ለፊት

ስልክ፡- 0111114800

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት
የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
The school seeks to procure office and teaching materials, maintenance items, electronics, cleaning supplies, uniforms, printing, fixed assets, photocopier repair, uniform sewing, and laboratory equipment via open tender. Bidders must submit a renewed business license, government supplier registration certificate, VAT registration, and item samples.
Save Tender