Tender Detail

Tender Details

  • Company በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 አፍንጮበር ጤና ጣቢያ
  • Address ከሰሜን ሆቴል ጀርባ ሲሲ ኤፍ ግቢ አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111-26-592-92
  • Website
  • Deadline12 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300(ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 2% ከባንክ በተመሰከረ CPO
  • opening dateበዛው እለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል
  • Categories Pharmaceutical Products , Medical Equipment And Supplies , Stationery Materials

የአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ የ2019 በጀት አመት የ1ኛ ዙር አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎች. የደንብ ልብሶች፣ ህትመቶች፣ የህክምና መለዋወጫ እቃዎች፣ መድሀኒቶች፣ ቋሚ እቃዎች፣ የልብስ ስፌቶች፣ የጥገና እቃዎች የአገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 አፍንጮበር ጤና ጣቢያ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አ. ጤ. ጣ ለ 01/2019

የአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ የ2019 በጀት አመት የ1ኛ ዙር አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎች. የደንብ ልብሶች፣ ህትመቶች፣ የህክምና መለዋወጫ እቃዎች፣ መድሀኒቶች፣ ቋሚ እቃዎች፣ የልብስ ስፌቶች፣ የጥገና እቃዎች የአገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

  1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለውን የዘመኑን ግብር ከፋይና እና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር የአቅራቢነት ምዝገባ ያለው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር ሰነዱ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ ፤ ጨረታው በ11ኛ ቀን 4፡00 ሰአት ታሽጎ በዛው እለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
  4. ተጫራቾች ያሸነፉአቸውን እቃዎች ወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ ንብረት ክፍል ሙሉ ወጪውን ችለው ማስረከብ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ ማስረከቢያ ብር 2% ከባንክ በተመሰከረ CPO ማስያዝ አለባቸው፤ ሙሉ ዝርዝር መረጃው ከሰነዱ ላይ መመልከት አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው ፡፡
  7. ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም ፡፡
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. የጨረታ ሰነድ መሰረዝ መደለዝ እና በፍሉድ መነካትአይቻልም፡፡
  10. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  11. ተጫራቾች በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ / ማስገባት አለባቸው፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች ላቀረበበት እቃ ሲፒኦ ካላሲያዘ ተቀባይነት የለውም፡፡
  13. ተጫራቾች የፎቶ ሳምፕሎች ከምሳፕል እቃ ጋር መቅረብ አለባቸው፡፡
  14. ጥቃቅን እና አነስተኛ በተደራጁበት መስክ ደብዳቤ አጽፈው የማምጣት ግዴታ አለባቸው፡፡

አድራሻ፡- አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ ከስሜን ሆቴል ጀርባ ሲ.ሲ ኤፍ ግቢ አጠገብ

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0111-25-07-44 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ

✨ messages.ai_summary
Afnhcho Ber Health Station seeks suppliers for stationery, cleaning materials, uniforms, printed materials, medical supplies, medicines, fixed assets, tailoring, and maintenance items via open tender. Bidders need a valid business license, tax and VAT registration, and Ministry of Finance supplier registration. Samples required.
Save Tender