በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የቦሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ቦሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
1ኛ ዙር ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የቦሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች
- የደንብ ልብስ ግዥ ሎት1
- ለአላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት 2
- ለአላቂ የት/ት እቃዎች ሎት3
- አላቂ የጽዳት እና ሌሎች ዕቃዎች ሎት4
- ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ ሎት5
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ሎት6
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል::
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ::
- የገቢዎች እና ጉምሩክ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት::
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት /ቫት/ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
- የአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር መያዝ የሚችሉ መሆን አለበት::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 300 ብር/ ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ቦሪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሰነዱን መግዛት ይቻላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን ይኸውም ሎት1 /የደንብ ልብስ ግዥ 30,000፣ ሎት2 /ለአላቂ የቢሮ ዕቃዎች 20,000፣ ሎት3 /ለአላቂ የት/ት ዕቃዎች 20,000፣ ሎት4/አላቂ የፅዳት እና ሌሎች ዕቃዎች 20,000፣ ሎት5 /ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ 50,000፣ ሎት6 /ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች 20,000 በባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ አለበት::
- የመወዳደሪያ ዋጋው ከነቫት በማስቀመጥ በግልጽ ተጠቅሶ መጻፍ ይኖርበታል::
- የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ዋናውንና ኮፒ በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: በተጨማሪም የሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና /specification/ ማቅረብ አለባቸው::
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከታወቀ በኋላ በ15 ቀናት ውስጥ ከት/ቤቱ ጋር ውል መዋዋል አለበት::
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ደረጃውን የጠበቀ ዕቃዎችን ትዕዛዙ በደረሳቸው በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ በናሙናው መሰረት አጠናቀው ለት/ቤቱ ንብረት ክፍል ሲያስረክቡ በጥራት ኮሚቴ ተረጋግጦ ሲያልፍና በተቋሙ ኃላፊ ገቢ እንዲሆን ከታዘዘ በኋላ ይከፍላቸዋል::
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4:00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ይታሸግና በዛው ዕለት በ4:30 ሰዓት ቦሪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ን/አ/የቡድን መሪ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ C.P.O በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ሁሉም ተጫራቾች ከጥር 1 ቀን ጀምሮ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለሥልጣን ባወጣው መመሪያ መሰረት ካሽ ሬጅስተር ያለው ወይም QR ኮድ ያለው ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው::
አድራሻ:- ከአያት አደባባይ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ በግራ በኩል በመናፈሻ ፊትለፊት 300 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል::
በለሚኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት
ቦሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Bori Secondary School seeks suppliers for office and educational supplies via open tender, split into six lots: uniforms, consumable office items, consumable educational items, cleaning supplies, fixed electronics, and fixed office items. Bidders must meet tax, licensing, customs clearance, VAT, and supplier registration requirements.
