Tender Detail

Tender Details

  • Company ሜልባ ፕሪንቲንግ ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ
  • Address ቦሌ ሚካኤል ኢጃ ዴቬሎፐር ህንጻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +2510118550083
  • Website
  • Deadline14 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300 ብር (ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Securityየአጠቃላይ ኮንትራት ዋጋ 1% ግን ከ 500,000.00 ብር ያልበለጠ
  • opening date04/02/2019 ከጠዋቱ 4:00
  • Categories Vehicle tire

የተሽከርካሪ ጎማዎች ግዥ – የጨረታ ቁጥር ሜልባ/ብ/ግ/ጨ/005/2019 – ሜልባ ፕሪንቲንግ ፓብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ

ሜልባ ፕሪንቲንግ ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: ሜልባ/ብ/ግ/ጨ/005/2019

ሜልባ ፕሪንቲንግ፣ፓብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለተለያዩ መኪኖች የሚያገለግሉ የተሽከርካሪ ጎማዎችን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የእቃው ዓይነት መለኪያ ብዛት
1 ጎማ ቁጥር : 7.50X16 (የ ፊት ለፊት ጎማ ቀጫጭን ጥርስ) ቁጥር 8
2 ጎማ ቁጥር : 7.50X16 (የ ኋላ ጎማ ወፍራም ጥርስ) ቁጥር 16
3 ጎማ ቁጥር : 185/65R15 ቁጥር 12
4 ጎማ ቁጥር : 155/80R13 ቁጥር 4
5 ጎማ ቁጥር : 185/70R14 ቁጥር 4

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን: የአጠቃላይ ኮንትራት ዋጋ 1% ግን ከ 500,000.00 ብር ያልበለጠ

የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት: 04/02/2019 ጠዋቱ 4:00

የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት: 04/02/2019 ከጠዋቱ 4:00

በዚህ መሰረት፡-

  1. በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች አግባብነት ያለው የዓመቱ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት፣ በጨረታው መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም የአቅራቢዎች ምዝገባ (suppliers list) ላይ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ዋና ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከድርጅቱ መ/ቤት የግዥ ዳይሬክቶሬት 2ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዋናውንና ቅጅ በተለያየ ፖስታ በማሸግና ሁሉንም በአንድ ላይ በሚይዝ በስም በታሸገ ፖስታ ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከ ተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ በአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት 2ኛ ህንጻ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
  6. አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ሜልባ ፕሪንቲንግ ፓብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ

አድራሻ፡- ሸገር/ ገላን ከተማ ልዩ ቦታ ገላን 30(ባጃጅ ተራ አካባቢ)

ለተጨማሪ መረጃ ፡ ስ.ቁ.+251 0118550083/+251911968780

ፊንፊኔ/ኢትዮጵያ

 

✨ messages.ai_summary
Melba Printing, Publishing and Packaging invites bidders to supply vehicle tires for various vehicles, including sizes 7.50X16, 185/65R15, 155/80R13 and 185/70R14. Bidders must submit a valid business license, VAT and tax registration, tax clearance, supplier registration certificate, and a CPO or unconditional bank guarantee.
Save Tender