Tender Detail

Tender Details

  • Company የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address አዳማ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-211-1873
  • Website
  • Deadline10 Oct 2026, 9:45 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateበዚያው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Categories Machinery , Disposal Sale

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት በታክስ ዕዳ የያዛቸውን የበቆሎ መፍጫ ማሽን ለመሸጥ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁ.03/2018

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት በታክስ ዕዳ የያዛቸውን የበቆሎ መፍጫ ማሽን ለመሸጥ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር ከፋይ የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው በታክስ አከፋፈል እዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተወጠው ስልጣን መሠረት አግዲ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዘ ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኝ የበቆሎ መፍጫ ማሽን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. ጨረታው የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ (ፓስፖርት) ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ በማሸግ በግልጽ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 ሰዓት - 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት 2:00 - 6፡00 ሰዓት ከቴሌ ከፍ ብሎ ቅጽ ቤቱ አዲስ ባስነባው ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይኖርበታል፡፡
  3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ 1/ስሰኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ስም (Ministry of Revenue Adama Branch Office) በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡
    ተ.ቁ የመ/ቤቱ ስም ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት የንብረቶቹ መመልከቻ ቀን የጨረታው የመዝጊያ እና የመከፈቻ ቀንና ሰዓት
    1 ገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅርንጫፍ የበቆሎ መፍጫ ማሽን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታ መክፈቻ ቦታ:- በገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ከቴሌ ከፍ ብሎ ባስገነባው አዲሱ ሕንጻ 4ኛ ፎቅ ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳዳር ቢሮ ቁጥር 403 ሲሆን ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ታዛቢዎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
  6. የግልጽ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ 16ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልጽ ጨረታው መከፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል፡፡
  7. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፈሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቶች ደግሞ የግልጽ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀናት ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያፃስፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ በሚሰጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ሀብት ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡
  9. ከላይ በተ.ቁ7 በተገለጸው ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልጽ ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በ CPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  10. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልጽ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡- 022-211-1873/ 022-211-1728 እና 022-211-4010 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Ministry of Revenue Adama Branch Office is selling a corn grinder seized for tax debt, located in Bishoftu town, on an as-is basis via open bid. Bidders must submit an ID or passport copy with the tender document and pay a non-refundable fee to obtain it.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender