Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 0335510693
  • Website
  • Deadline29 Sep 2026, 9:50 AM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 100 (አንድ መቶ)
  • Bid Security200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር ወይም 100,000 /መቶ ሺህ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO)
  • opening date4፡00 ሰዓት
  • Categories Cloth And Shoes , Used Items , Cosmotics

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ አልባሳት፣ ኮስሞቲከስ፣ ጫማ፣ የሞባይ ከቨር፣ የሞባይል ቻርጀር፣ ማስቲካ፣ ላፕቶፕ፣ የባጃጅ ጎማ፣ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 8/2019

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ አልባሳት፣ ኮስሞቲከስ፣ ጫማ፣ የሞባይ ከቨር፣ የሞባይል ቻርጀር፣ ማስቲካ፣ ላፕቶፕ፣ የባጃጅ ጎማ፣ modified epoxy risen anchoring HM-500 390ml: structural airing adhesive HM120ml carbon fiber impegnated 20kg adhesive HM-180c3p structural repairing esive HM120ml Hm-180ce/20kg በግልፅ እንድዉም ኮስሞትክስ እና ኤሌከትሮኒከስ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ ለመሸጥ ይፈልጋል፤ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹ

  1. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ከሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ሲሆን ተሸከርካሪ መጫረት ለምትፈልጉ ንግድ ፈቃድ የማይጠይቅ በመሆኑ ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ የኗሪነት መታወቂያ ያለው ግለሰብ መጫረት ይችላል።
  2. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ግለሰብ መጫረት ይችላል።
  3. የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 2 ሚሊየን በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ የምስከር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ማቅረብ አያስፈልገውም፡፡
  4. በጨረታ የሚሸጠው እቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
  5. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው (6) ቀን 3፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታው የዕቃዎችን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው እና በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፁትን በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልፅ ጨረታው 3፡50 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሀራጅ ጨረታው 4፡30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል።
  8. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመከፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል፤ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃው እንደገና ለጨረታ ይቀርባል፡፡
  9. ተጫራቾች ለእቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሸናፊ ከሆኑ ተጨማሪ ዕሴት ታከስ 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ እቃዎችን በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እና ስድስተኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ድረስ ማመልከት ይችላሉ።
  11. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ እቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሀራጅ ጨረታ የእቃው መነሻ ዋጋ ከ 2 ሚሊየን ብር በላይ ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እንድሁም የእቃው መነሻ ዋጋ ከ 2 ሚሊየን ብር በታች ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 /መቶ ሺህ/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 033 551 06 93 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Customs Commission's Kombolcha branch is selling assorted confiscated goods—clothing, cosmetics, shoes, mobile covers and chargers, laptops, and more—via open and auction-style bids. Bidders need a valid business license, VAT registration, tax clearance, and TIN; individuals 18+ with ID may bid for vehicles.
Save Tender