የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት በ2019 በጀት ዓመት ከውስጥ ገቢ በአስፓልት መሃል ላይ ላለው ሚዲያ በውስጡ የተተከለው ሳር እንዳይደርቅ ውሃ ጠዋትና ማታ ለማጠጣት የሻወር ትራክ ለአንድ ዓመት በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት በ2019 በጀት ዓመት ከውስጥ ገቢ በአስፓልት መሃል ላይ ላለው ሚዲያ በውስጡ የተተከለው ሳር እንዳይደርቅ ውሃ ጠዋትና ማታ ለማጠጣት የሻወር ትራክ ለአንድ ዓመት በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
1. የማሽነሪ ኪራይ ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች በ2018 ዓ.ም የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ (ክሊራንስ ያላቸው) በክልል ወይም በፈዴራል በክልሉ ንግድ ኢንዱስትሪ ቢሮ ወይም መምሪያ በአቅራቢነት የተመዘገቡ፣ ህጋዊ ብቃት ያላቸው እና ማረጋገጫና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የጨረታ ማስከበሪያ /BID Security/ 80,000 /ሰማንያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ መዘዣ (CPO) ወይም unconditional bank guarantee ማቅረብ ይኖርበታል።
2. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በሥራ ወቅት ከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው አከራዮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም።
3. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በይርጋዓለም ከተማ በፕሮጀክቱምሆነበመደበኛ በጀት ሥራ ውል ስምምነት ገብተው ሥራ ጀምረው ያላጠናቀቁ (ያልጨረሱ) ተቋራጮች ጨረታውን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም።
4. በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውን ተ.ዕ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ብር በመክፈል ደረሰኛቸውን በመያዝ ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾቹ ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት ሳይቱ በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።
6. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond security)፣ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡30 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።
7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 5፡30 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 9፡30 ላይ ይከፈታል፣የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
8. አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል።
10. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
11. በጨረታ አከፋፈት ሥነ-ሥርዓት ላይ የተነበበው ዋጋ አርቴሜትክ ቼክ በሚደረግበት ጊዜ በሁለቱም መካከል ያለው ከ2% በላይ በታች ከሆነ ቀጥታ ከጨረታ ውጭ ይደረጋል።
12. የቀረበው ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒው የማይታይ እና የማይነበብ ከሆነ እንዲሁም የሚያጠራጥር ሁኔታ ቢገኝ ኦርጅናሉን የማቅረብ ግዴታ አለበት።
13. በጨረታ ላይ ያለው ጠቅላላ ዋጋ ከማንድስ ግምት /ከወቅቱ ከገበያ ዋጋ 15% በላይ ከሆነ እና ከ 30% በታች ከቀረበ የወቅቱ የገበያ መዋዠቅ እና የስራውን አንገብጋቢነት በማስቀደም ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ልማት ጽ/ቤት
