Tender Detail

Tender Details

  • Company የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
  • Address , Phone: 0111240249
  • Website
  • Deadline06 Oct 2026, 4:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200 /ሁለት መቶ ብር/ የማይመለስ
  • Bid Securityያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO)
  • opening dateከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታተይ ቀናት
  • Categories Wood And Wood Working , Disposal Sale , Forest And Tree Sales

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የቁም ደን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት


ለመጀመርያ ጊዜ የወጣ

የቁም ደን ሸያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር OFWE/GU-02/2019

 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ፊንፊኔ ቅ/ጽ/ቤት ጅባት ጌዶ ድስትሪክት፤ ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጋራሙልታ እና ጀርሶ ጉርሱም ዲስትሪክቶች ፤ ጅማ ቅ/ጽ/ቤት ስግሞ ሰጠማ እና በቢያ ፎላ ዲስትሪክቶች ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ፤ በወለጋ ቅ/ጽ/ቤት ቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ድስትሪክቶች ላይ የፈረንጅ ጥድ እና የ”Gravelea robusta” ግንድላ እና ባሌ ቅ/ጽ/ቤት አሎሼ ባቱ ድስትሪክት ላይ የፈረንጅ ጥድ እና የባህር ዛፍ ድብልቅ ግንድላ እንዲሁም ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት ሲቦ ቶሊ ቆቦ ድስትሪክት ላይ የዝርያዎች ድብልቅ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

1.      የግንዲላ እና የእንጨት መሰንጠቂያ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የቫት (VAT) ተመዝጋቢና “TIN number” ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል ኦይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 እና ጨረታው በወጣበት ፈንፊኔ ቅ/ጽ/ቤት ፊንፊኔ ከተማ፤ ባሌ ቅ/ጽ/ቤት ጎባ ከተማ ፤ ወለጋ ቅ/ጽ/ቤት ጊምቢ ከተማ፤ ሀራርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጭሮ ከተማ፤ ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት መቱ ከተማ እና ጅማ ቅ/ጽ/ቤት ጅማ ከተማ በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ።

2.    ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታተይ ቀናት ይቆይል።

3.    ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል።

4.    ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የምትጫረቱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች፣ በቅ/ጽ/ቤት የምትጫረቱ መ/ቤቱ ከሚገኝበት ከተማ በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO)ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

5.    ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0111240249 በመደወል መጠየቅ ወይም www.oromiaforest.et ድህረ ገፅ ማጎብኘት ይችላሉ።

 

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት

✨ messages.ai_summary
The Oromia Forest and Wildlife Enterprise is selling standing forest (timber) from various districts via open bid. Eligible bidders must have a renewed trade license for timber and sawmilling, VAT registration, and a TIN. The enterprise may cancel the tender in part or full.
Save Tender

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ እንደሚከተለው አቅርቧል፡፡

READ MORE