በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጌዴኦ ዞን የኮቾሬ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለኮቾሬ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት እና በሥሩ ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች የሚውል ሞተር ሳይክሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጌዴኦ ዞን የኮቾሬ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለኮቾሬ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት እና በሥሩ ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች የሚውል ሞተር ሳይክሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።
1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡-
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡-
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑ
4. የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡-
5. የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡-
6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ 50,000/ሃምሳ ሺህ/ ብር ማስያዝ የሚችል ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኮ/ወ/ፋይናንስ ስም አሰርተው ማቅረብ የሚችል፡-
7. የጨረታ ሠነድ በማይመለስ 200/ ሁለት መቶ / ብር መግዛት የሚችሉ፡-
8. ከአሰሪ መስሪያ ቤት ጋር በሚገባው ውል መሠረት በጨረታ ያሸነፉትን ሞተር ሳይክሎችን እስከ መጋዘን ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
9. የግዥው መጠን ከ ሃያ ሺህ ብር በላይ ከሆነ መ/ቤቱ የቫቱን ግማሽ ፐርሰንት ቆርጦ የሚያስቀር መሆኑ ይታወቅ፡-
10.አሸናፊው ውል ገብቶ ወደ ሥራ ከመገባቱ በፊት የዉል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅበታል።
11.መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሠነድ በኮቾሬ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 01 ከ12/01/2019 ዓ/ም እስከ 02/02/2019 ዓ/ም ድረስ እየተሸጠ ቆይቶ በ16 ኛዉ የሥራ ቀን ላይ በ03/02/2019 ዓ/ም ዕለተ ማክሰኞ ከረፋዱ 05፡00 ሰዓት ላይ የመጫረቻ ሠነድ ኦርጂናሉንና የማይመለስ አንድ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እናት/ፖስታ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ገብቶ በዕለቱ ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል።
ለበለጠ መረጃ 046-366-0433/ +251 91 692 0261/ +251 91 663 4937
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት
በጌዴኦ ዞን የኮቾሬ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት
