የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በያዘው እቅድ መሰረት፡-
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በያዘው እቅድ መሰረት፡-
ሎት 1 ለጽ/ቤቱ ተሽከርካሪ መኪናዎች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የቀላል መኪና ጎማዎችና የከባድ መኪና ጎማ ግዥ፤ ሎት 2 የደንብ ልብስ ግዢ ለመፈጸም በማቀድ የወጣ የግልጽ ጨረታ የተጫራቾች መመሪያ ነው።
- በግልጽ ጨረታ ዋጋ ማቅረቢያቸው ላይ የድርጅታችሁን ስም፣ አድራሻችሁን ስልጣን በተሰጠው የድርጅቱ ኃላፊ ፈርማችሁን እና ህጋዊ ማህተማችሁን በማሳረፍና የዋጋ ማቅረቢያውን ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ካብኔ ጉዳዮች ጽ/ቤት በማለት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ለግልጽ ጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ መመሪያ በደንብ ማንበብ ዋጋ ሲሞላ ከሚደርሰው ስህተት ያድናል፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያ ሲሞላ ስህተት ቢኖረው የግልጽ ጨረታ ሳጥኑ ከመታሸጉ በፊት ስህተቶቹን በጽሑፍ በማረምና በሌላ ፖስታ በማድረግ ፖስታው ላይ የተሻሻለ ወይም የተለወጠ የሚል ጽሑፍ ጽፎ በግልጽ ጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ሌሎች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም አቅርቦ ቢገኝ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
- የግልጽ ጨረታ ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያቸው ላይ የሚሰጡት በግልጽ ጨረታው የሚያቀርቡትን የተወዳደሩበትን ዕቃ ዓይነት፣ መለኪያ እና የአንዱን ዋጋ መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ መሆን ይገባዋል።
- የዋጋ ማቅረቢያ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እንዲኖረው አይፈቀድም፣ በእርሳስ እና በቀይ እስክርቢቶ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ግልጽ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ያቀረበውን ዋጋ መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ውድድሩን ትቻለሁ ቢል ለግልጽ ጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ይቀጣል እንደ አስፈላጊነቱም መ/ቤቱ ወደ ፊት በሚያወጣው ግልጽ ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ሊያደርግ ይችላል።
- ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አሸናፊ የሆኑባቸውን የዕቃ አቅርቦት ዋጋ በግልጽ ጨረታ ሰነዶች ላይ ባቀረቡት ዋጋ ብቻ ለመ/ቤታችን ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በዝርዝር በተገለጹት የዕቃ ዓይነቶች ባላቸው የፍቃድ አይነት የዕቃ አይነቶች በሙሉ ሆነ በከፊል መወዳደር ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የግልጽ ጨረታውን ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ በግልጽ መረዳትና በተግባር ላይ ማዋል አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የዕቃ ሽያጭ ዋጋ ሁኔታ መ/ቤቱ በጠየቀው እስፔስፍኬሽን መሠረት መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑ ግብር የተከፈለበትን የቫት ተመዝጋቢና የምስከር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ከዋናው ሰነዳቸው ጋር እያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ግልጽ ጨረታው በአየር ላይ ከሚቆይበት ቀናቶች ውጪ ዘግይተው የሚቀርቡ የዋጋ ማቅረቢያ
- ግልጽ ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በመጨረሻ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በማስታወቂያ ከወጣበት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8:10 ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ግልጽ ጨረታው በተጫራቾች ፊት በግልጽ ይነበባል፣ የግልጽ ጨረታ አከፋፈት ዝርዝር ቃለ ጉባዔ ተይዞ በመ/ቤቱ ጨረታ ኮሚቴ ይፈረማል እንዲሁም በግልጽ ጨረታው አከፋፈቱ ላይ የተገኙ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በግልጽ ጨረታው አከፋፈት ስነ ስርዓት ላይ ስለመገኘታቸው እንዲፈራረሙ ይደረጋል፡፡
- የአገልግሎት ጊዜው መ/ቤት የግልጽ ጨረታውን አሸናፊውን ከለየ በኋላ ለአሸናፊው ድርጅት በጽሁፍ ያሳውቃል፡
- የአገልግሎት ጊዜው መ/ቤት የግልጽ ጨረታ አሸናፊውን ለይቶ ካላወቀ በኋላ በ3 ቀናት ውስጥ በቀረበው ዋጋ መሰረት ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ይገባል።
- የግልጽ ጨረታን በሚመለከት ጨረታውን ለማሸነፍ እንዲረዳው ለማንኛውም ኃላፊ እና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከግልጽ ጨረታው የሚሰረዝ እና አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ የሚሰረዝ መሆኑንና በህግ የሚያስቀጣው እንደሆነ ማወቅ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የግልጽ ጨረታን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ለእያንዳንዱ ሎት ሲፒኦ (C.P.O) 20,000 /ሃያ ሺህ/ ማስያዝ ይኖርበታል ቢድ ቦንድ ማስያዝ ፈጽሞ አይፈቀድም።
- በዚህ የግልጽ ተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን ያልፈጸመ በተራ ቁጥር 19 ላይ የተመለከተውን የጨረታ ማስከበሪያ ሊያስቀጣው ይችላል።
- ተጫራቾች በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ በማያያዝ ግልጽ ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ቤ/ጉ/ክልል አሶሳ ከተማ በሚገኘው በጽ/ቤቱ ግዢና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 104 በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ግልጽ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ሁሉም ተጫራቾች ግልጽ ጨረታው ከሚከፈትበት ቀን በፊት ሙሉ በሙሉ የግልጽ ጨረታ ሰነዳቸውን ቀድመው ካስገቡ የጨረታ መክፈቻ ጊዜውን ሳይጠብቅ ለተጫራቾች በስልክ ጥሪ ተደርጎ ይከፈታል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ አሶሳ ከተማ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ካብኔ ጉዳዮች ጽ/ቤት ግዢና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል።
አድራሻ ስልክ ቁጥር 09 21-17-78-90/057-775-24-99/057-775-0142/057-775-00-31/09 15-89-09-36
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender by the Benishangul-Gumuz Regional Chief Administrator's Office for Lot 1: light and heavy vehicle tires, and Lot 2: uniforms. Bidders need a renewed business license and VAT registration certificate. Bidders may compete for all or part of the listed items.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
