ጨረታ ቁጥር (1) ለእንጨትና ብረታ ብረት ለትምህርትና ስልጠና ስራዎች አገልግሎት የሚውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል
የጨረታ ማስታወቂያ
የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል
ጨረታ ቁጥር (1) ለእንጨትና ብረታ ብረት ለትምህርትና ስልጠና ስራዎች አገልግሎት የሚውል የጥሬ ዕቃ ግብዓቶች፣ የቧንቧ ዕቃዎች፤ የተለያዩ ለትምህርት እና ለንባብ አገልግሎት የሚውሉ መጽሐፎች ጨረታ ቁጥር (2) የሲቪል ሰራተኞች፤ የስፖርተኞች የሥራ ልብስና ጫማዎች እንዲሁም በህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውል ዩኒፎርም ብትን ጨርቅ፣ የእንስሳት መኖ ግብዓቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ፣ በሥራው መስክ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በዕቃ ግዢና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበት የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ እና መለያ ቁጥር (Tim Number) ተመዝጋቢ የሆኑና የተሟላ ማስረጃ በ4 ኮፒ በማድረግ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን አንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመሰስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000007971188 አ/አ ማረ/ቤት እደ-ጥበባት ማዕከል በሚል ገንዘቡን ገቢ በማድረግ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል ግዥ ክንውን ቡድን 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ ማ/ቤቱ የሚገዛቸውን ዕቃዎች ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ተዘርዝሮ ቀርቧል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በጨረታ ቁጥር 1-2 ለተጠቀሱት ጨረታዎች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚመለስ ለእያንዳንዳቸው ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
- ተጫራቾች አንዱ በሌላው ተጫራች ሰነድ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ናሙና እንዲያቀርቡ የተጠየቀባቸው ናሙናውን በጨረታ መከፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነድ መግዛትና የመተዳደሪያ ሃሳባቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አሽገው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ቁጥር 1 መስከረም 26/2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዕለቱ በ4፡15 ሰዓት በማረ/ቤቱ በግዥ ክንውን ቢሮ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ቁጥር 2 መስከረም 27/2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በዕለቱ በ4፡15 ሰዓት በማ/ቤቱ አደራሽ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል ገላን በሚገኘው ዕቃ ግ/ቤት አምጥተው ያስረክባሉ፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ማረሚያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ፕሮፎርማቸው ላይ ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ የሌለበት ጎላ ብሎ የሚነበብ ፅሑፍ መሆን ይገባዋል፤ ስርዝ ድልዝ ያለበት ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡ በአሃዝና በፊደል መፃፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡
አድራሻ፦ የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል ገላን
የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል
✨ messages.ai_summary
Supply of raw materials, plumbing items, books, uniforms, sportswear, footwear, animal feed and related goods for education and training. Bidders need a valid business licence, tax clearance, MoFED supplier registration, VAT and TIN registration, and must submit samples where requested.
