Tender Detail

Tender Details

  • Company በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በፐ/ሰ/የሰ/ል ጽ/ቤት/አስ/ፋ/ፑል የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን
  • Address Addis Ababa Ethiopia, Phone: ------
  • Website
  • Deadline18 Sep 2026, 7:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200 /ሁለት መቶ/ ብር
  • opening dateበ5ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Categories Office Supplies And Services , Printing And Publishing , Vehicles Rent

በአራዳ ከፍለ ከተማ አስተዳደር በፐ/ሰ/የሰ/ል ጽ/ቤት/አስ/ፋ/ፑል የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ለራሱና በስሩ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- አ/ክ/ከ/አ/ፐ/ሰ/የሰ/ል/አስ/ፋ/T/የመ/ግ/አስ/01/2018/19

በአራዳ ከፍለ ከተማ አስተዳደር በፐ/ሰ/የሰ/ል ጽ/ቤት/አስ/ፋ/ፑል የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ለራሱና በስሩ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች
  • ሎት 2 የደንብ ልብስ
  • ሎት 4 የጥገና ዕቃዎች
  • ሎት 5 የህትመት አገልግሎቶች
  • ሎት 6 የፎቶ ኮፒና ፕሪንት ቀለም
  • ሎት 7 የመኪና ኪራይ
  • ሎት 8 የአይቲ ዕቃዎች
  • ሎት 9 ድንኳን ኪራይ
  • ሎት 10 የመኪና ጎማ
  • ሎት 11 የመኪና ልዩ ልዩ ማስዋብ
  • ሎት 12 የቀላል መኪና ጥገና

ስለሆነም በጨረታው ተሳትፎ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. ተጫራቶች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ፤ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ፡ በወቅቱ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣ የምስክር ወረቀት ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ የመለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቶች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ብር መክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በፐ/ሰ/የሰ/ል/ጽ/ቤት/አስ/ፋ/ፑል የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ጽ/ቤት የከፍያ ሂሳብ ደጋፊ የስራ ሂደት 6ኛ ፎቅ በመቅረብ ሰነድ ከገዙ በኋላ እዛው 6ኛ ፎቅ ከመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ክፍል ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

ተጫራቾች ለጨረታ የሚወዳደሩበትን እያንዳንዱ ሎት ወይም የበጀት ርዕስ በሲፒኦ ብር

  • ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎች (5,000.00 ብር)
  • ሎት 2 የደንብ ልብስ (5,000.00 ብር)
  • ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች (5,000.00)
  • ሎት 4 የጥገና ዕቃዎች (5,000.00 ብር)
  • ሎት 4 የጥገና ዕቃዎች (5,000.00 ብር)
  • ሎት 5 የህትመት አገልግሎቶች (10,000.00 ብር)
  • ሎት 6 የፎቶ ኮፒና ፕሪንት ቀለም (10,000.00 ብር)
  • ሎት 7 የመኪና ኪራይ (15,000.00 ብር)
  • ሎት 8 የአይቲ ዕቃዎች (15,000.00 ብር)
  • ሎት 9 የድንኳን ኪራይ (5,000.00 ብር)
  • ሎት 10 የመኪና ጎማ (40,000.00 ብር)
  • ሎት 11 የመኪና ልዩ ልዩ ማስዋብ (5,000.00 ብር)
  • ሎት 12 የቀላል መኪና ጥገና (35,000.00 ብር)
  1. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥርና የዕቃውን ዓይነት በግልጽ ኤንቨሎፕ ላይ በመጻፍና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በአራዳ ከፍለ ከተማ አስተዳደር በፐ/ሰ/የሰ/ል/ጽ/ቤት/አስ/ፋ/ፑል የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ጽ/ቤት የመንግስት የግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማስገባት አለባቸው።
  2. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ4ኛው ቀን 1፡00 ሰዓት ተዘግቶ በቀጣዩ በ5ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት የጨረታው ሣጥን ተጫራቶች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በአራዳ ከፍለ ከተማ አስተዳደር በፐ/ሰ/የሰ/ል/ጽ/ቤት አስ/ፋ/ፑል የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 6ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
  • የጨረታው መዝጊያና መከፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ይከፈታል።
  1. ተጫራቶች ጨረታው ከመከፈቱ 1 ቀን በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ዕቃዎች በሙሉ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ናሙናው ለማይቀርብባቸው የዕቃ ዓይነቶች በተቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የአገልግሎት ስራዎችን በተመለከተ ከድርጅቱ ጋር በመሄድ የሚታይ ይሆናል።
  2. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ጥሬ ዕቃዎች የእያንዳንዱን ነጠላ ዋጋ ድምር ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ጨምሮ ማካተት ይኖርባቸዋል።
  3. ጽ/ቤቱ ጨረታውን ለመገምገም የሚጠቀምባቸው መስፈርቶች ዕቃዎቹ መ/ቤቱ ባስቀመጠው ስፔስፍኬሽን መሰረት መሆናቸውን ወይም በሚቀርበው ናሙና፣ ጥራት፣ ዋስትና፣ አነስተኛ ዋጋ አጠቃሎ ለሚያቀርብ ጊዜ ግምት ውስጥ ይገባል።
  4. ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  5. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም። አድራሻ- በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አራዳ ክፍለ ከተማ በፐ/ሰ/የሰ/ል/ጽ/ቤት/አስ/ፋ/ፑል የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 6ኛ ፎቅ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ ብርሃንና ስላም ንግድ ባንክ ፊት ለፊት ነው።

ስልክ ቁጥር፡- 011-12-65-3-24

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በፐ/ሰ/የሰ/ል ጽ/ቤት/አስ/ፋ/ፑል የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን

✨ messages.ai_summary
Open tender for office supplies, uniforms, cleaning and maintenance items, printing services, photocopy/print ink, vehicle rental, IT equipment, tent rental, tires, vehicle decoration, and light vehicle maintenance. Bidders need a valid trade license, tax clearance, supplier registration, VAT and TIN certificates, and must submit samples.
Save Tender