Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት
  • Address ወላይታ ሶዶ ፣ኢትዮጲያ, Phone: ----------
  • Website
  • Deadline16 Oct 2019, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceየጨረታ ሰነድ መግዧ ብር መጠን አልተገለጸም፡፡
  • opening dateጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6:00 ሰዓት
  • Categories Machinery , Sales, Disposals And Foreclosure

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞናሊቲ አቶ ሱማሞ ዶባሞ ኢርግቾ በዱቤ ግዥና ኪራይ ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛው በውሉ መሰረት የኪራይ ክፍያ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የዳቦ ማምረቻ ማሽነሪ ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል፡፡


የዝግ ጨረታ  ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞናሊቲ አቶ ሱማሞ ዶባሞ ኢርግቾ በዱቤ ግዥና ኪራይ ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛው በውሉ መሰረት የኪራይ ክፍያ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የዳቦ ማምረቻ ማሽነሪ ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል፡፡

 

ተ.ቁ የተከራዩ ስም የሚሸጠው ንብረቱ ዓይነት እና ዝርዝር መረጃ ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የዝግ ጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር) ዝግ ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ ዝግ ጨረታ ሚካሄድበት ቀንና ሰዓት የጨረታ ሁኔታ
1. አቶ ሱማሞ ዶባሞ ኢርግቾ 1.Rotary Oven 16 Try (01) set 2. Volumetric Dough Divider  የሊጥ ማከፋፈያ (01) set 3. Mixer የሊጥ መቀላቀያ  (01) set 4. Moulder የሊጥ ቅርጽ ማውጫ (01) set 5. Bread slicer የዳቦ መቁረጫ አንድ (01) set 6. French bread tray and trolley for ATDF 250 ሁለት (02) set 7. Flat tray with Trolley for ATDF 250 ሁለት (02) 8. Diesel Generator አንድ (01) set ናቸው ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሀዲያ ዞን፣ ሆሳዕና ከተማ አስ/ር፣ በአራዳ ቀበሌ ውስጥ በአቶ ሱማሞ ዶባሞ በተቋቋመው የዳቦ ማምረቻ ቦታ፣ 9,792,010.52 ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሀዲያ ዞን፣ ሆሳዕና ከተማ አስ/ር፣ በአራዳ ቀበሌ ውስጥ በአቶ ሱማሞ ዶባሞ (የተከራይ) የዳቦ ማምረቻ ቦታ፣ ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6:00 ሰዓት ዝግ ጨረታ

 

የዝግ ጨረታው መመሪያ

  1. በዝግ ጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ስምና አድራሻ በመጥቀስ፤ የታደሰ መታወቂያ ኮፒ፤ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 4% ወይም 25% በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ገዢው የሚገዛበትን ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ድረስ ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል፡፡
  2. ንብረቱ የሚገኘው ሆሳዕና ከተማ አስ/ር፤ በአራዳ ቀበሌ ውስጥ በተከራይ ማምረቻ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው፡፡ የዝግ ጨረታ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT)፤ ንብረቶችን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሸያጭ የሚገዛ ከሆነ ከቀረጥ ነጻ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግስት/በሕግ የተወሰነ ታክስ ጨምሮ የሚጠየቁ ማንኛውንም ክፍያ በቅድሚያ በመክፈል ንብረቱን ይረከባል፡፡
  3. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ/በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን ይረከባል፡፡ በዝግ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግስት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የጉምሩክ ቀረጥ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ ሁሉ በዝግ ጨረታ መሳተፍ ይችላል፡፡
  4. ንብረቱን በከፊል ለመከራየት የሚፈልግ ተጫራች ከሆነ ቢያንስ ያሸነፈበትን ዋጋ 20% ቅድሚያ በመክፈልና የባንኩን የሊዝ ክራይ መስፈርት በማላት በ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡ ግዴታውን ካልተወጣ የዝግ ተጫራች አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል። ለተሸነፉ ተጫራቾች በጨረታው ያስያዙት የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመሰስላቸዋል፡፡
  5. ንብረቱ በባንኩ የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት መሰረት የመከራየት ዕቅድ ያለው ተጫራች የባንኩን ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ በቅድሚያ እርግጠኛ መሆንና በባንኩ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት ባንኩ የሚያከናውነው የፕሮጀክቱ ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ-ሁኔታዎች መስማማት ይጠበቅበታል፡፡ የዝግ ጨረታ አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ንብረቱን ለማስተዳደር የሚወጡ ተያያዥ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ ይጠበቅበታል፡፡
  6. የዝግ ጨረታ አሸናፊ የካፒታል ዕቃው ካለበት ቦታ ወደ ሚፈለግበት ቦታ የማጓጓዣ ወጪ፤ የጉዞ ኢንሹራንስ፤ ስራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው ይከፍላል፡፡
  7. የዝግ ጨረታው ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪል በተገኘበት ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6:00 ሰዓት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ሎን ወርክአውት ዲቪዥን ቢሮ ይደረጋል፡፡ ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-180-1528/38 ደውሎ ማነጋገር ይችላል።
  8. ንብረቶቹን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዝግ ጨረታ ቀን በፊት ባሉት ጊዜያት ቀጠሮ በመያዝ ንብረቶቹ በሚገኙበት በተከራይ ማምረቻ ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይቻላል። ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የዝግ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። በተጨማሪም ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ በመከፈልና የባንኩን የካፒታል ዕቃ ኪራይ መስፈርት በማሟላት በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ የማሸነፊያ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ግን በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ማሟላት ባይችል የዝግ ጨረታው ይሰረዛል፡፡

የኢትዮጲያ ልማት ባንክ ወላይት ሶዶ ዲስትሪክት

✨ messages.ai_summary
Ethiopia Development Bank, Wolaita Sodo District, seeks to sell or lease bakery machinery (rotary oven, dough divider, mixer, moulder, bread slicer, trays, trolleys, generator) via closed bid after the lessee defaulted. Open to individuals, institutions, or SMEs; VAT and customs duties apply unless exempt.
Save Tender