በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡ/ከ/አስ/ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ለከተማው ፓትሮል አገልግሎት የሚውል ፒካፕ ደብል ጋቢና ተሽከርካሪ በ2019 በጀት ዓመት በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ አከራዮችን አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፤
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/19
በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡ/ከ/አስ/ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ለከተማው ፓትሮል አገልግሎት የሚውል ፒካፕ ደብል ጋቢና ተሽከርካሪ በ2019 በጀት ዓመት በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ አከራዮችን አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፤
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው እና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በአከራይነት ማስረጃ ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክርነት ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
- የተሽከርካሪው አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊክሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር/ብቻ በመክፈል ከግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ጠቅላላ ዋጋ 10,000/አስር ሺህ ብር/ በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቡ/ከ/አስ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡ/ከ/አስ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
- የተሽከርካሪ አይነትና ሞዴል በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ማግኘት ይቻላል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0913 971 760 / 0973 807 293 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የቡ/ከ/አስ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት
ቱለፋ
አድራሻ፣ ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሀን በሚወስደው መንገድ ከአዲስ አበባ 65 ኪ.ሜ ርቀት ከፍቼ ከተማ አለፍ ብሎ እንገኛለን።
በአብክመ በሰ/ሸዋ ዞን የቡልጋ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ፋ/ን/አስ/ቡድን
✨ messages.ai_summary
The Bulga Town Administration Peace and Security Office seeks to rent a pickup double-cabin vehicle for city patrol service, selecting among legally licensed renters. Bidders must have a renewed business license, TIN, and VAT registration certificate proving rental eligibility.
