Tender Detail

Tender Details

  • Company ወገግታ የልጆች የበጎ አድራጎት ድርጅት
  • Address , Phone: 09 10 67 26 14
  • Website
  • Deadline11 Sep 2026, 5:02 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price
  • opening dateጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
  • Categories Accounting & Auditing

ወገግታ የልጆች የበጎ አድራጎት ድርጅት ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው።


የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ

ወገግታ የልጆች የበጎ አድራጎት ድርጅት ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው። ከሀምሌ 01/2017 እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም አመታዊ ሂሳብ ለማስመርመር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ የሂሳብ ባለሞያዎች በጨረታው አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ተጫራቾች፡

  • የንግድ ፍቃድ ያለው /ያላት
  • በሙያው ብቃትና ህጋዊነት ታውቀው በመንግስት የተመዘገቡ
  • የዘመኑን ግብር ከፍለው ፈቃዳቸውን ያደሱ
  • የኦዲቲንግ የስራ ልምድ ያላቸው
  • የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው

መስፈርቱን የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች ሊመረመር የተዘጋጀው መዝገብ 1 ቦክስ ፋይል በመሆኑ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለአገልግሎት የምታስከፍሉትን ዋጋ እና ስራውን ሰርታችሁ የምታስረክቡበትን ጊዜ በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ውስጥ በአካል ቀርቦ የዋጋ ተመን እና ሰርቶ የማጠናቀቂያ ጊዜ እንድታሳውቁ እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ፡- 09 10 67 26 14/ 0911 91 57 11 መደወል ትችላላችሁ።

አድራሻ፡- አራት ኪሎ አራዳ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት ኤልሳ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 503

ወገግታ የልጆች የበጎ አድራጎት ድርጅት

Save Tender