የኮልፌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የኮልፌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም
የኮልፌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት.1-የደንብ ልብስ ግዥ እና የስፌት አገልግሎት ፤ሎት.2-አላቂ የቢሮ እና የትምህርት ዕቃዎች፤ ሎት.3-ህትመት ሎት.4-አላቂ ህከምና ዕቃ ሎት 5-ለአላቂ ፅዳት ዕቃዎች ሎት.6-ልዩ ልዩ አጋዝ መፅሀፍቶች በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ሎት.7- ቋሚ ዕቃዎች : ሎት.8-የተለያዩ የጥገና ስራዎች እና ዕቃዎች ሎት.9- የጄኔሬተር ጥገና እና ዕቃ የፕሪንተሮች እና ፎቶ ኮፒ የማባዥ ማሽኖች ሰርቪስ (የቢሮ ዕቃዎች ጥገና)፤ ሎት10-የመኪና ጥገና፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ሎት፡-11 ለቤተ ሙከራ የሚሆኑ ኬሚካሎች ዕቃዎች ሎት 12-ቆሎ እና ኩኪስ ሎት13- የመኪና ኪራይ አገልግሎት ሎት-14 ለመምህራን እና ሰራተኞች ካፌ አገልግሎት ስራማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስስዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ
በተጫራቾች መመሪያ
1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ከአገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የዘመኑ የመንግስት ግብርየከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እንዲሁም የአቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች የሚሸጡበትን የአንዱን ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመግልጽ አርጅናልና ፎቶ ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታ ዓይነት በግልፅ በመጻፍ እንዲሁም ተሞሉቶ የዋጋ ዝርዝር ጋር መደበኛ የጨረታ ሰነዱ ሙሉ በሙሉ መመለስ አለበት፡፡ የጨረታ ሰነዱ ካልተመለሰ የጨረታ ውድድሩ ላይ መቅረብ የማይችሉ መሆኑን እየገለፅን በአግባቡ የተሞላውን የጨረታ ሰነድ ለዚሁ ተበሎ በተዘጋጀው የኮልፌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ/ግ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 የጨረታ ሳጥን መግባት ይኖርበታል።
3. ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ ስማቸውን ፤ አድራሻቸውንና ፤ ፊርማቸውን በእያንዳዱ ሰነድ ላይበመፈረም ማቅረብ አለባቸው ሰነዶቹ በማህተም መረጋገጥ አለባቸው።
4. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት እቃዎችን ከግዥ አስተዳደሩ ጋር በሚገባው ውል መሰረት እንዲያስገባ ሲታዘዝ እቃ ግምጃ ቤታችን ድረስ በራሱ ወጪ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
5. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ እቃዎች ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች የመ/ቤቱ የእቃ ጥራት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ የእቃዎችን ጥራት አይቶ መ/ቤቱ ካወጣው የጨረታ ሰነድ እና በጨረታው እንዲያልፍ ከተደረገው የእቃ ቴክኒካል ስፔስፊኬሽንና ከቀረበው ናሙና ጋር የማይጣጣም ከሆነና ጥራት የጎደለው ነው ብሎ ካመነ ጨረታውን አሸንፎ እቃ እንዲያቀርብ የታዘዘው/ድርጅት/እቃውን እንዲመልስ ማድረግ ይችላል።
7. በጨረታው ያሸነፈ አካል ማሸነፍ እንደተገለፀለት ከመ/ቤቱ ጋር በ15 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መፈፀም አለበት፡፡
8. የግዥ ውል የሚፈፀምበት ጊዜ ሰነዱ ላይ የተሰጠው የእቃ ብዛት በተወሰነ መጠን ሊጨምርም ወይም ሊቀንስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ አውቆ የመጫረት ግዴታ አለበት፡፡
9. ተጫራቾች ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ቀደም ብለው ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ናሙና ቢሮ ቁጥር 6 ማስረከብ አለባቸው፡፡
10. የሚሸጠው የጨረታ ሰነድ የማይመለሰ ብር200.00 /ሁለት መቶ ብር መከፈል ይኖርበታል፡፡
11. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀንጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይሲሆን በ11ኛ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
12. የጨረታ መዝጊያና መከፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
13. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የተጠቀሰውን ብር ከታወቀ ባንከ በcpo አሰርታችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የእያንዳንዱ ሎት በጀትን የተሰላው በዐ.5% ነው።
15. የጥቃቅን እና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች የሚያመርቱትን ምርት የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
|
ሎት1 |
ሎት2 |
ሎት3 |
ሎት4 |
ሎት5 |
ሎት6 |
ሎት7 |
ሎት8 |
ሎት9 |
ሎት10 |
ሎት11 |
ሎት12 |
ሎት13 |
ሎት14 |
|
12400 |
18800 |
15000 |
1000 |
12000 |
1000 |
1400 |
4000 |
2400 |
1500 |
1100 |
1000 |
2400 |
11000 |
ለበለጠ መረጃ አድራሻ
ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍስ ከተማ ወረዳ 11 በ18 ሱኳንዳ ወደ አሸዋ ሜዳ በሚወስደው መንገድ ደገኛል፡፡
ስልክ ቁጥር -011-2790012/011-2-592157
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምርህርት ቢሮ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የኮልፌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
