Tender Detail

Tender Details

  • Company የመስከረም ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከስኛ ደ/ት/ቤት
  • Address Addis Ababa Ethiopia, Phone: 0115-579371/ 50115-571602
  • Website
  • Deadline03 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price100.00 (አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityበእያንዳንዱ ሎት (CPO) 5000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ)
  • opening dateበ4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  • Categories Furniture And Furnishing , Printing And Publishing , Textile, Garment & Leather

የመስከረም ቅድመ እንደኛ፤ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ሎት1 የደንብ ልብሶች ሎት2.

የመስከረም ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከስኛ ደ/ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 1/2019 ዓ.ም

የመስከረም ቅድመ እንደኛ፤ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ሎት1 የደንብ ልብሶች ሎት2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት3. የተለያዩ ህትመቶች ሎት4 አላቂ የህክምና እቃዎች ሎት5 አላቂ የትምህርት እቃዎች ሎት6 ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ሎት7. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ሎት8. የሰራተኞች የመዝናኛ ከበብ (የመስተንግዶ) ሎት9. ቋሚ ዕቃዎች ሎት10. የህንፃ ቁሳቁሶች ሎት11 የውሃ የመብራት የበር የመስኮት ጥገና ሎት12. የተለያዩ የኮምፒውተር፣ የላፕቶፕ፣ የፕሪንተር የማባዣ፣ የፎቶ ኮፒ፣ የኢንተርኔት ዝርጋታ ጥገናዎች ሎት13. የደንብ ልብስ ስፌት አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት ለመወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር የከፈሉ በአቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተመሰከረለት በእያንዳንዱ ሎት (CPO) 5000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን በማየት ናሙና የሚቀርብባቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታውን የሚያሸንፈው ድርጅት ዕቃዎችን እስከ ት/ቤቱ ድረስ ማድረስ አለበት፡፡
  5. ጨረታው እየር ላይ የሚቆይበት ግዜ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆንና በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  6. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚያቀርቡት እቃ ወይም ምርት ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጁ ዕቃዎችን ገዝተው ለሚወዳደሩበት እንደማንኛውም ተጫራቶች ጨረታ ሰነድ መግዛትና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ስርዝ ድልዝ የማይነበብ ሰነድ ጨረታ ላይ ያልተነበበ የዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራቶች ላለፉባቸው እቃዎች 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ቫትን ጨምሮ በፖስታ ታሽጎ በፋይናንስ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0115-579371 እና 0115-571602 በመደወል እንዲሁም በአካል አድራሻ፡- ግቢ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ጀርባ በስታ ጤና ጣቢያ አጠገብ በመምጣት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 08 መስከረም ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከልኛ ደ/ት/ቤት
  • ገቢ ገብርኤል ጀርባ ባሕታ ጤና ጣቢያ አጠገብ
  • ስልክ ቁጥር 0115-579371 50115-571602

የመስከረም ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከስኛ ደ/ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for supply of uniforms, office furniture, printing, medical, educational and other goods, equipment, building materials, repairs, and maintenance services across 13 lots. Bidders must hold valid licenses, tax clearance, VAT registration, and provide samples before bid opening.
Save Tender